ሕዝቅኤል 31:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 በክብርና በታላቅነት ከዔድን ዛፎች መካከል እንግዲህ ማንን ትመስላለህ? ሆኖም ከዔድን ዛፎች ጋር ወደ ታችኛው ምድር ትወርዳለህ፥ በሰይፍ በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ትጋደማለህ። ይህም ፈርዖንና ብዛቱ ሁሉ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 “ ‘በዔድን ካሉት ዛፎች በውበትና በትልቅነት የሚወዳደርህ የትኛው ነው? ይሁን እንጂ አንተም እንደዚሁ ከዔድን ዛፎች ጋራ ከመሬት በታች ትወርዳለህ፤ በሰይፍ ከተገደሉት፣ ካልተገረዙትም መካከል ትጋደማለህ። “ ‘እንግዲህ ፈርዖንና ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝቡ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 “ዛፉ የግብጽ ንጉሥና የሕዝቡ ሁሉ ምሳሌ ነው፤ በዔደን ገነት ከነበሩት ዛፎች መካከል እንኳ በቁመትና በውበት እርሱን የሚያኽል አልነበረም። አሁን ግን በዔደን ገነት እንደ ነበሩት ዛፎች ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳል፤ እዚያም በእግዚአብሔር የማያምኑ በጦርነት ከተገደሉት ሁሉ ጋር ይደባለቃል፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 “በክብርና በታላቅነት በዔድን ዛፎች መካከል ማንን ትመስላለህ? ነገር ግን ከዔድን ዛፎች ጋር ወደ ታችኛው ምድር ያወርዱሃል፤ በሰይፍም በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ትተኛለህ። ይህም ፈርዖንና የሕዝቡ ብዛት ሁሉ ነው፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 በክብርና በታላቅነት በዔድን ዛፎች መካከል ማንን መስለሃል? ነገር ግን ከዔድን ዛፎች ጋር ወደ ታችኛው ምድር ያወርዱሃል፥ በሰይፍም በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ትተኛለህ። ይህም ፈርዖንና የሕዝቡ ብዛት ሁሉ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። Ver Capítulo |