በዚያም ዖዴድ የተባለ የጌታ ነቢይ ነበረ፤ ወደ ሰማርያም የሚመጣውን ጭፍራ ሊገናኘው ወጣ፥ እንዲህም አላቸው፦ “እነሆ፥ የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ ይሁዳን ስለ ተቈጣ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣቸው፥ እናንተም ወደ ሰማይ በሚደርስ ቁጣ ገደላችኋቸው።
ኤርምያስ 51:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባቢሎንን ልንፈውሳት ሞከርን፥ እርሷ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሏልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ አገራችን እንሂድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ባቢሎንን ለመፈወስ ሞክረን ነበር፤ እርሷ ግን ልትፈወስ አትችልም፤ ፍርዷ እስከ ሰማይ ስለ ደረሰ፣ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ስላለ፣ ትተናት ወደየአገራችን እንሂድ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ የሚኖሩ የውጪ አገር ሰዎች እንዲህ አሉ፦ ‘ባቢሎንን ልንፈውሳት ሞከርን፤ እርሷ ግን ልትፈወስ አልቻለችም፤ የተፈረደባት ፍርድ እስከ ደመና ድረስ ከፍ ስላለና ከዚያም በላይ እስከ ሰማይ ድረስ ስለ ደረሰ ትተናት እያንዳንዳችን ወደየሀገራችን እንሂድ።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባቢሎንን ፈወስናት፥ እርስዋ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ከዋክብትም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ እንተዋት፤ ሁላችንም ወደ ሀገራችን እንሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባቢሎንን ፈወስናት፥ እርስዋ ግን አልተፈወሰችም፥ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎአልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ አገራችን እንሂድ። |
በዚያም ዖዴድ የተባለ የጌታ ነቢይ ነበረ፤ ወደ ሰማርያም የሚመጣውን ጭፍራ ሊገናኘው ወጣ፥ እንዲህም አላቸው፦ “እነሆ፥ የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ ይሁዳን ስለ ተቈጣ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣቸው፥ እናንተም ወደ ሰማይ በሚደርስ ቁጣ ገደላችኋቸው።
እንዲህም አልሁ፦ “አምላኬ ሆይ፥ አፍሬአለሁ፤ አምላኬ ሆይ፥ ፊቴንም ወደ አንተ ለማንሣት እፈራለሁ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ከፍ ብሏልና፥ በደላችንም ወደ ሰማያት ወጥቷልና።
የደከምሽባቸው ነገሮች እንዲህ ይሆኑብሻል፤ ከሕፃንነትሽ ጀምረው ከአንቺ ጋር ይነግዱ የነበሩ እያንዳንዳቸው ወደ ስፍራቸው ይሄዳሉ፥ የሚያድንሽ አይገኝም።
እርሱም ብዙዎችን አሰነካከለ፥ እርሱም ደግሞ ወደቀ፤ እርስ በርሳቸውም፦ ተነሡ፥ የአስጨናቂው ሰው ከሆነው ሰይፍ ፊት ወደ ወገናችን ወደ ተወለድንባትም ምድር እንመለስ ተባባሉ።
በእርሷም መካከል ያሉ ቅጥረኛ ወታደሮችዋ እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የጥፋታቸው ቀንና የመጐብኘታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና ተመለሱ፥ በአንድነትም ሸሹ፥ አልቆሙምም።
ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፤ የአስጨናቂው ሰው ከሆነው ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል።