Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 47:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የደከምሽባቸው ነገሮች እንዲህ ይሆኑብሻል፤ ከሕፃንነትሽ ጀምረው ከአንቺ ጋር ይነግዱ የነበሩ እያንዳንዳቸው ወደ ስፍራቸው ይሄዳሉ፥ የሚያድንሽ አይገኝም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከልጅነት ጀምሮ ዐብረሻቸው የደከምሽው፣ ዐብረሽ የተገበያየሻቸው፣ ሊያደርጉ የሚችሉት ይህንኑ ብቻ ነው። እያንዳንዱ በስሕተቱ ይገፋበታል፤ አንቺን ግን የሚያድን የለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከወጣትነትሽ ጀምሮ ከአንቺ ጋር ለመጠንቈል ይመላለሱ የነበሩት አስማተኞችም ሁሉ እንደዚሁ በተሳሳተ መንገድ ይባክናሉ፤ ስለዚህ አንቺን ማንም ሊያድንሽ አይችልም።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እነ​ርሱ ረዳ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ጀም​ረሽ ደከ​ምሽ፤ ሰው በራሱ ይሳ​ሳ​ታል፤ ለአ​ንቺ ግን መድ​ኀ​ኒት የለ​ሽም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የደከምሽባቸው ነገሮች እንዲህ ይሆኑብሻል፥ ከሕፃንነትሽ ጀምረው ከእንቺ ጋር ይነግዱ የነበሩ እያንዳንዳቸው ወደ ስፍራቸው ይሄዳሉ፥ የሚያድንሽም የለም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 47:15
8 Referencias Cruzadas  

መብል የሚወዱ ከቶ የማይጠግቡ ውሾች ናቸው፤ እረኞቹም ማስተዋል የማይችሉ ናቸው፤ ሁሉም ወደ መንገዳቸው ዞሩ፥ ከፊተኛው እስከ ኋለኛው ድረስ ሁሉ፥ እያንዳንዳቸው ወደ ጥቅማቸው ዘወር ብለዋል።


ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤ እንደ አንበሳ ደቦል ያገሣሉ፤ ያደኑትንም ይዘው ይጮኻሉ፤ ተሸክመውት ይሄዳሉ፤ የሚያስጥልም የለም።


እኔም አምላክ ነኝ፥ ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፤ እሠራለሁ፥ የሚከለክልስ ማን ነው?


በጫንቃቸው ላይ አንሥተው ይሸከሙታል፤ በስፍራውም ያደርጉታል፥ በዚያም ይቆማል፤ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይሰማውም ከመከራውም አያድነውም።


በምክርሽ ብዛት ደክመሻል፤ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፥ ከዋክብትንም የሚመለከቱ፥ በየመባቻውም የሚመጣውን ነገር የሚናገሩ ተነሥተው ከሚመጣብሽ ነገር ያድኑሽ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios