ኤርምያስ 51:55 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ባቢሎንን አጥፍቶአታልና፥ ከእርሷም ታላቁን ድምፅ ዝም አሰኝቶአልና፤ ሞገዳቸውም እንደ ብዙ ውኆች ይተምማል፥ የድምፃቸውም ጩኸት ያስገመግማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ባቢሎንን ያጠፋታል፤ ታላቅ ጩኸቷንም ጸጥ ያደርጋል። ሞገዳቸው እንደ ታላቅ ውሃ ይተምማል፤ ጩኸታቸውም ያስተጋባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ባሕር ሞገድ የሚያስገመግም ሠራዊት በድንገት በባቢሎን ላይ ደርሶ እየደነፋ አደጋ ይጥልባታል፤ በዚህም እኔ አጠፋታለሁ፤ ጸጥም አደርጋታለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ባቢሎንን አጥፍቶአታልና፥ ከእርስዋም ሞገዱ እንደ ብዙ ውኃዎች የሚተመውን ታላቁን ድምፅ ዝም አሰኝቶአልና፤ የድምፃቸው ጩኸት ተሰምቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ባቢሎንን አጥፍቶአታልና፥ ከእርስዋም ታላቁን ድምፅ ዝም አሰኝቶአልና፥ ሞገዳቸውም እንደ ብዙ ውኆች ይተምማል፥ የድምፃቸውም ጩኸት ተሰምቶአል። |
ሕዝቦች እንደ ብዙ ውኃ ጩኸት ይጮኻሉ፤ እርሱ ግን ይገሥጻቸዋል፤ እነርሱም እየሸሹ ይርቃሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ በነፋስ ፊት፥ ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረውም ትቢያ ይበተናሉ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፥ ባሕር ሞገድን እንደሚያስነሣ እንዲሁ ብዙ ሕዝቦችን አስነሣብሻለሁ።