ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ እንዲህም አሉት፦ “የዕብራውያን አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በፊቴ እራስህን ለማዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ።
ኤርምያስ 50:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም ሰው አያምልጥ፤ በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ በኩራት አልታዘዝም ብላለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ቀስት የሚገትሩትን፣ ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ፣ ዙሪያውን ሁሉ መሽጉ፤ የእስራኤልን ቅዱስ፣ እግዚአብሔርን አቃልላለችና፣ እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፤ በሌሎች ላይ እንዳደረገችውም አድርጉባት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቀስት መደገን የሚችሉትን ቀስተኞች በባቢሎን ላይ ይዘምቱ ዘንድ ጥሩአቸው፤ ከተማይቱን ይክበቡ፤ ማንም እንዳያመልጥ ተጠባበቁ፤ የክፉ ሥራዋንም ዋጋ ክፈሉአት፤ በሌሎች ላይ የፈጸመችውንም ግፍ በእርስዋም ላይ ፈጽሙባት፤ እርስዋ በእስራኤል ቅዱስ በእኔ ላይ ተዳፍራለች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ቀስትን የሚገትሩ ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት፤ ከእርስዋም ሰዎች አንድ አያምልጥ፤ የእስራኤልን ቅዱስ እግዚአብሔርን ተቃውማለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፤ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፥ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም አያምልጥ፥ በእስራኤል ቅዱስ ላይ በእግዚአብሔር ላይ ኰርታለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት። |
ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ እንዲህም አሉት፦ “የዕብራውያን አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በፊቴ እራስህን ለማዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ።
የተገዳደርኸው የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደርግህበት፥ ዓይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን!’
በክፋትሽ ታምነሻል፤ “የሚያየኝ የለም” ብለሻል፤ ጥበብሽና እውቀትሽ አታልለውሻል፥ በልብሽም፦ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ብለሻል።
በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ማሣቀቅያህና የልብህ ኩራት አታልለውሃል። ምንም እንኳ ጎጆህን እንደ ንስር ጎጆ ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል ጌታ።
ከየአቅጣጫው በእርሷ ላይ ኑ፥ ጎተራዎችዋንም ክፈቱ፤ እንደ ተቈለለ ነዶ ከምርዋት ፈጽማችሁም አጥፉአት፥ ምንም ዓይነት ነገር አታስተርፉላት።
እነሆ፥ ከሰሜን ምድር የታላላቅ አሕዛብን ጉባኤ አስነሣለሁ በባቢሎንም ላይ አመጣቸዋለሁ፤ በእርሷም ላይ ይሰለፋሉ፥ ከዚያም ትያዛለች፤ ፍላጾቻቸውም ተጨናግፎ ባዶውን እንደማይመለስ እንደ ብልህ ጀግና ፍላጻ ናቸው።
አጥፊው በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ኃያላኖችዋ ተያዙ፥ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ ጌታ ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና፥ ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል።
ጤት። አደፍዋ በልብስዋ ዘርፍ ነበረ፥ ፍጻሜዋን አላሰበችም፥ ስለዚህ በድንቅ ተዋርዳለች፥ የሚያጽናናትም የለም፥ አቤቱ፥ ጠላት ከፍ ከፍ ብሏልና መከራዬን ተመልከት።
እርሱም ሰው የሚያመልከውን ነገር ወይም አማልክት ነን ከሚሉት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግና በመቃወም፦ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ብሎ ያውጃል፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ ይቀመጣል።