Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 50:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “ቀስት የሚገትሩትን፣ ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ፣ ዙሪያውን ሁሉ መሽጉ፤ የእስራኤልን ቅዱስ፣ እግዚአብሔርን አቃልላለችና፣ እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፤ በሌሎች ላይ እንዳደረገችውም አድርጉባት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም ሰው አያምልጥ፤ በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ በኩራት አልታዘዝም ብላለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቀስት መደገን የሚችሉትን ቀስተኞች በባቢሎን ላይ ይዘምቱ ዘንድ ጥሩአቸው፤ ከተማይቱን ይክበቡ፤ ማንም እንዳያመልጥ ተጠባበቁ፤ የክፉ ሥራዋንም ዋጋ ክፈሉአት፤ በሌሎች ላይ የፈጸመችውንም ግፍ በእርስዋም ላይ ፈጽሙባት፤ እርስዋ በእስራኤል ቅዱስ በእኔ ላይ ተዳፍራለች፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 “ቀስ​ትን የሚ​ገ​ትሩ ቀስ​ተ​ኞ​ችን ሁሉ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጥሩ​አ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያዋ ስፈ​ሩ​ባት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ሰዎች አንድ አያ​ም​ልጥ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​ማ​ለ​ችና እንደ ሥራዋ መጠን መል​ሱ​ላት፤ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ችም ሁሉ አድ​ር​ጉ​ባት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፥ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም አያምልጥ፥ በእስራኤል ቅዱስ ላይ በእግዚአብሔር ላይ ኰርታለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 50:29
28 Referencias Cruzadas  

ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው እንዲህ አሉት፤ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ራስህን በፊቴ ለማዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ሕዝቤ ያመልኩኝ ዘንድ ልቀቃቸው።


የሰደብኸውና ያቃለልኸው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ከፍ ያደረግኸው፣ ዐይንህን በትዕቢት ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው እኮ!


በክፋትሽ ተማምነሽ፣ ‘ማንም አያየኝም’ አልሽ፤ ደግሞም፣ ‘እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌላ የለም’ ባልሽ ጊዜ፣ ጥበብሽና ዕውቀትሽ አሳሳቱሽ።


ሕዝቧም ለብዙ ሕዝቦችና ለታላላቅ ነገሥታት ባሮች ይሆናሉ፤ እንደ አድራጎታቸውና እንደ እጃቸውም ሥራ እከፍላቸዋለሁ።”


“እግዚአብሔርን ንቋልና፣ ሞዓብን በመጠጥ አስክሩት። ሞዓብ በትፋቱ ላይ ይንከባለል፤ ለመዘባበቻም ይሁን።


አንተ በዐለት ንቃቃት ውስጥ የምትኖር፣ የተራራውንም ከፍታ የያዝህ ሆይ፤ የምትነዛው ሽብር፣ የልብህም ኵራት አታልሎሃል፤ መኖሪያህን እስከ ንስር ከፍታ ቦታ ብትሠራም፣ ከዚያ ወደ ታች አወርድሃለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።


ባቢሎን ሆይ፤ ወጥመድ ዘርግቼልሻለሁ፤ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ እግዚአብሔርን ተገዳድረሻልና፣ ተገኘሽ፤ ተያዝሽም።


ከሩቅ መጥታችሁ በርሷ ላይ ውጡ፤ ጐተራዎቿን አፈራርሱ፤ እንደ እህል ክምር ከምሯት፤ ፈጽማችሁ አጥፏት፤ ምኗም አይቅር።


ትዕቢተኛው ይሰናከላል፤ ይወድቃልም፤ የሚያነሣውም የለም፤ በዙሪያው ያሉትን ሁሉ የሚበላ እሳት፣ በከተሞቹ ውስጥ አስነሣለሁ።”


የታላላቅ መንግሥታትን ማኅበር፣ ከሰሜን በባቢሎን ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱም በርሷ ላይ ይሰለፋሉ፤ መጥተውም ይይዟታል። ቀስቶቻቸው ባዶ እጃቸውን እንደማይመለሱ፣ እንደ ሥልጡን ተዋጊዎች ናቸው።


“በጽዮን ላይ ስላደረሱት ጥፋት ሁሉ ለባቢሎንና በባቢሎን ለሚኖሩት ሁሉ ዐይናችሁ እያየ ዋጋቸውን እከፍላቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።


ቀስተኛው ቀስቱን እስኪገትር፣ የጦር ልብሱንም እስኪለብስ ፋታ አትስጡት፤ ለወጣቶቿ አትዘኑ፤ ሰራዊቷንም ፈጽማችሁ አጥፉ።


“በምድር ሁሉ የታረዱት፣ በባቢሎን ምክንያት እንደ ወደቁ፣ ባቢሎንም በእስራኤል በታረዱት ምክንያት መውደቅ ይገባታል።


በባቢሎን ላይ አጥፊ ይመጣል፤ ጦረኞቿ ይማረካሉ፤ ቀስታቸውም ይሰበራል፤ እግዚአብሔር ግፍን የሚበቀል፣ ተገቢውንም ሁሉ የሚከፍል አምላክ ነውና።


ርኩሰቷ በቀሚሷ ላይ ታየ፤ ወደ ፊት የሚሆንባትን አላሰበችም፤ አወዳደቋ አስደንጋጭ ሆነ፤ የሚያጽናናትም አልነበረም፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ መከራዬን ተመልከት፤ ጠላት ድል አድርጓልና!”


እግዚአብሔር ሆይ፤ እጆቻቸው ላደረጉት፣ የሚገባውን መልሰህ ክፈላቸው።


“ንጉሡ ደስ እንዳለው ያደርጋል፤ ከአማልክት ሁሉ በላይ ራሱን እጅግ ከፍ በማድረግ በአማልክት አምላክ ላይ ተሰምቶ የማይታወቅ የስድብ ቃል ይናገራል፤ የቍጣውም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ይሳካለታል፤ የተወሰነው ነገር ሁሉ መሆን አለበትና።


የሰማይ አምላክ የሚያደርገው ሁሉ ትክክል፣ መንገዶቹም ሁሉ ጽድቅ ስለ ሆኑ፣ አሁንም እኔ ናቡከደነፆር እርሱን አወድሰዋለሁ፤ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፤ አከብረዋለሁም፤ እርሱም በትዕቢት የሚመላለሱትን ማዋረድ ይችላል።


ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ፣ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ የመቅደሱን መጠጫዎች አስመጣህ፤ አንተና መኳንንትህ፣ ሚስቶችህና ቍባቶችህም የወይን ጠጅ ጠጣችሁባቸው፤ ማየት፣ መስማት፣ ማስተዋልም የማይችሉትን የብርና የወርቅ፣ የናስና የብረት፣ የዕንጨትና የድንጋይ አማልክትን አመሰገንህ። ሕይወትህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ ግን አላከበርህም።


“በአሕዛብ ሁሉ ላይ፣ የእግዚአብሔር ቀን ደርሷል፤ አንተ እንዳደረግኸው፣ በአንተም ላይ ይደረጋል፤ ክፉ ሥራህም በራስህ ላይ ይመለሳል።


እግዚአብሔር ጻድቅ በመሆኑ መከራን ለሚያመጡባችሁ መከራን ይከፍላቸዋል፤


እርሱም አምላክ ከተባለና ከሚመለከው ነገር ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተቀምጦ፣ “እኔ አምላክ ነኝ” እያለ ዐዋጅ ያስነግራል።


የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ፣ አንተም ደግሞ ደም እንዲጠጡ አደረግሃቸው፤ ይህ የሚገባቸው ነውና።”


በሰጠችው መጠን ብድራቷን መልሱላት፤ ለሠራችው ሁሉ ዕጥፍ ክፈሏት፤ በቀላቀለችውም ጽዋ ዕጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos