Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 47:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በክፋትሽ ታምነሻል፤ “የሚያየኝ የለም” ብለሻል፤ ጥበብሽና እውቀትሽ አታልለውሻል፥ በልብሽም፦ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ብለሻል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በክፋትሽ ተማምነሽ፣ ‘ማንም አያየኝም’ አልሽ፤ ደግሞም፣ ‘እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌላ የለም’ ባልሽ ጊዜ፣ ጥበብሽና ዕውቀትሽ አሳሳቱሽ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “በክፋትሽ ተዝናናሽ፤ ‘ማንም አያየኝም’ አልሽ፤ ጥበብሽና ዕውቀትሽ አባከኑሽ፤ በልብሽም ‘ማንም እንደኔ ያለ የለም’ አልሽ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በክ​ፋ​ትሽ ታም​ነ​ሻል፤ አንቺ ግን፥ “እኔ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ የለም” ብለ​ሻል፤ በዝ​ሙ​ትሽ ኀፍ​ረት ያሰ​ብ​ሽ​ው​ንም ዕወቂ፤ በል​ብሽ፥ “እኔ ነኝ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም” ብለ​ሻ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በክፋትሽ ታምነሻል፥ የሚያየኝ የለም ብለሻል፥ ጥበብሽና እውቀትሽ አታልለውሻል፥ በልብሽም፦ እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም ብለሻል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 47:10
23 Referencias Cruzadas  

በልቡም እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፥ ፈጽሞም እንዳያይ ፊቱን ሰወረ”።


ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፥ ከድንኳንም ይነቅልሃል ያፈልስሃልም፥ ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።


ንጹሕንም በስውር ለመንደፍ ቀስትን ገተሩ፥ ድንገት ይነድፉታል አይፈሩምም።


መንፈስን ለማገድ በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፥ በሞቱም ቀን ላይ ሥልጣን የለውም፥ በጦርነትም ውስጥ መሰናበቻ የለም፥ ክፋትም ሠሪውን አያድነውም።


እናንተም፦ “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፥ ከሲኦልም ጋር ተማምለናል፤ ሐሰትን መሸሸጊያችን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም” ስላላችሁ፥


ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከጌታ ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፦ “ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል?” ለሚሉ ወዮላቸው!


አመድ ይበላል፥ የተታለለ ልብ አስቶታል፥ ነፍሱን ለማዳን አይችልም፥ ወይም፦ “በቀኝ እጄ ሐሰት አለ?” ብሎም አይጠይቅም።


አሁንም አንቺ ተድላን የምትወጅ፥ በምቾትም የምትቀመጪ፥ በልብሽም፦ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም፥ የወላድ መካንነትንም አላውቅም” የምትዪ ይህን ስሚ፤


ራሳቸውን እንደ ብልኅ ለሚቈጥሩ፤ በራሳቸውም አመለካከት ጥበበኛ ለሆኑ ወዮላቸው!


በጽድቅ የሚጠራ በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በእርባና ቢስ ነገር ታምነዋል ሐሰትንም ተናግረዋል፤ ጉዳትን ፀንሰዋል በደልንም ወልደዋል።


ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ይላል ጌታ። ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል ጌታ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።


ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።


ጥበበኞች ነን ሲሉ ሞኞች ሆኑ፤


የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነት ነው። እንደተጻፈውም፥ “እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል፤”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos