ስለዚህ አክዓብ አራት መቶ የሚሆኑትን ነቢያቱን ጠርቶ “ወደ ራሞት ሄጄ አደጋ ልጣልባት ወይስ ልተው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “ሄደህ አደጋ ጣልባት፤ ጌታም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲሉ መለሱለት።
ኤርምያስ 5:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ወድደዋል፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወድዳሉ፤ ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነቢያት ነን የሚሉት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናቱ በነቢያት ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቡም ይህን ሁሉ አይቃወሙም፤ ታዲያ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ በሚደርስበት ጊዜ ምን ይበጃችሁ ይሆን?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፥ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ? |
ስለዚህ አክዓብ አራት መቶ የሚሆኑትን ነቢያቱን ጠርቶ “ወደ ራሞት ሄጄ አደጋ ልጣልባት ወይስ ልተው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “ሄደህ አደጋ ጣልባት፤ ጌታም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲሉ መለሱለት።
በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?
በዚያም ቀን በዚች ባሕር ዳርቻ የሚቀመጡ፥ ‘እነሆ፥ ከአሦር ንጉሥ እንድን ዘንድ ለእርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፤ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ይላሉ።”
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፤ አምላክ የሌላቸው በፍርሃት ራዱ፤ “ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ? ለዘለዓለምም ከምትነድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ?”
ምድሪቱ የምታለቅሰው፥ የአገሩ እጽዋት ሁሉ የሚደርቀው እስከ መቼ ነው? የተቀመጡባት ሰዎች፦ “ፍጻሜያችንን አያይም” ብለዋልና ስለ ክፋታቸው እንስሶችና ወፎች ተጠራርገው ጠፍተዋል።
ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “ነቢያቱ በስሜ የውሸትን ትንቢት ይናገራሉ፤ አላክኋቸውም፥ አላዘዝኋቸውም፥ አልተናገርኋቸውም፤ የውሸትን ራእይ ምዋርትንም ከንቱንም ነገር የልባቸውንም ሽንገላ ይሰብኩላችኋል።
ጤት። አደፍዋ በልብስዋ ዘርፍ ነበረ፥ ፍጻሜዋን አላሰበችም፥ ስለዚህ በድንቅ ተዋርዳለች፥ የሚያጽናናትም የለም፥ አቤቱ፥ ጠላት ከፍ ከፍ ብሏልና መከራዬን ተመልከት።
ኖን። ነቢዮችሽ ከንቱና ሐሰተኛ ራእይ አይተውልሻል፥ ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፥ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል።
በነፋስና በውሸት የሚሄድ፥ ሐሰትንም የሚናገር፥ “ስለ ወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ስብከት እናገርልሃለሁ” የሚል ሰው ቢኖር፥ እርሱ የዚህ ሕዝብ ሰባኪ ይሆናል።
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፥ ነቢዮችዋ በብር ያሟርታሉ፤ “ጌታ በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር በእኛ ላይ አይመጣብንም” እያሉ በጌታ ይደገፋሉ።