ሽብር ይይዛቸዋል፤ ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤ እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።
ኤርምያስ 48:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተሞቹ ተይዘዋል፥ አምባዎቹም ተወስደዋል፥ በዚያም ቀን የሞዓብ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ሆኖአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተሞቹ ይወረራሉ፤ ምሽጎቹም ይያዛሉ፤ በዚያ ቀን የሞዓብ ጦረኞች ልብ፣ በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተሞችና ምሽጎች ሁሉ ይያዛሉ፤ በዚያን ጊዜ የሞአብ ወታደሮች በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ሆነው በፍርሃት ይጨነቃሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐቄርዮት ተያዘች፤ አንባዎችዋም ተወስደዋል፤ በዚያም ቀን የሞአብ ኀያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተሞቹ ተይዘዋል፥ አምባዎቹም ተወስደዋል፥ በዚያም ቀን የሞዓብ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል። |
ሽብር ይይዛቸዋል፤ ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤ እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።
እንደታመመች የበኩርዋንም እንደምትወልድ ሴት የጭንቀት ድምፅ ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ታቃስታለች፥ እጆችዋንም በመዘርጋት፦ “በነፍሰ ገዳዮች ፊት ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ!” አለች።
እነሆ፥ እንደ ንስር ወጥቶ ይበራል ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፥ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።”
ሰይፍ በፈረሶችዋና በሰረገሎችዋ ላይ በመካከልዋም ባሉት በባዕድ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፥ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍም በመዝገቦችዋ ላይ አለ እነርሱም ይበዘበዛሉ።
የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኃይላቸውም ደክሙአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መቀርቀሪያዎችዋም ተሰብረዋል።
እነርሱም፦ “ሰላምና ደኅንነት ነው” በሚሉ ጊዜ ምጥ እንደ ያዛት እርጉዝ ሴት ድንገተኛ ጥፋት በእነርሱ ላይ ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።