ኤርምያስ 46:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ እነሆ፥ አንተን ከሩቅ ዘርህንም ከተማረከባት ምድር አድናለሁና፤ ያዕቆብም ተመልሶ ያርፋል በደኅንነትም ይቀመጣል፥ እርሱንም ማንም አያስፈራውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤ እስራኤል ሆይ፤ አትሸበር፤ አንተን ከሩቅ ስፍራ፣ ዘርህንም ተማርኮ ከሄደበት ምድር አድናለሁ። ያዕቆብም ተመልሶ በሰላምና በርጋታ ይቀመጣል፤ የሚያስፈራውም አይኖርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የአገልጋዬ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! አትፍሩ ተስፋም አትቊረጡ፤ እናንተን ከሩቅ አገር፥ ዘራችሁንም ከተማረኩበት ምድር እታደጋለሁ። እናንተም እንደገና ማንም ሳያስፈራችሁ በሰላምና በደኅንነት ትኖራላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ነገር ግን አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ እነሆ አንተን ከሩቅ፥ ዘርህንም ከተማረኩባት ምድር አድናለሁ፤ ያዕቆብም ተመልሶ ያርፋል፤ ተዘልሎም ይተኛል፤ ማንም አያስፈራውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ፥ አትፍራ፥ አንተም እስራኤል ሆይ፥ አትደንግጥ፥ እነሆ፥ አንተን ከሩቅ ዘርህንም ከተማረከባት ምድር አድናለሁ፥ ያዕቆብም ተመልሶ ያርፋል ተዘልሎም ይቀመጣል፥ ማንም አያስፈራውምም። |
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ።
ከእናንተም ዘንድ ታገኙኛላችሁ፥ ይላል ጌታ፤ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፥ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ካሳደድሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ እናንተንም ለምርኮ ካፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ።
እነሆ፥ በቁጣዬና በመዓቴ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት አገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፥ በደኅንነትም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤
በምድሪቱም ከሚሰማው ወሬ የተነሣ ልባችሁ የዛለ አይሁን አትፍሩም፤ በአንዱም ዓመት አንድ ወሬ፥ በሚቀጥለውም ዓመት ሌላ ወሬ ይመጣል፥ በምድሪቱም ላይ ዓመጽ ይሆናል፥ ገዢም በገዢ ላይ ይነሣል።
ምርኮአቸውን እመልሳለሁ፤ የሰዶምና የሴቶች ልጆችዋን ምርኮ፥ የሰማርያንና የሴቶች ልጆችዋን ምርኮ፥ በመካከላቸው ያለውን የአንቺንም ምርኮ እመልሳለሁ፥
የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፥ የፈረሱትንም ከተሞች ዳግም ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁንም ይጠጣሉ፤ የአትክልት ስፍራዎችንም ያበጃሉ፥ ፍሬውንም ይበላሉ።