ኤርምያስ 29:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ከእናንተም ዘንድ ታገኙኛላችሁ፥ ይላል ጌታ፤ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፥ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ካሳደድሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ እናንተንም ለምርኮ ካፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እኔም እገኝላችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከምርኮም እመልሳችኋለሁ፤ እናንተንም ከበተንሁበት አገርና ስፍራ ሁሉ እመልሳችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በምርኮ ምክንያት ወዳስለቀቅኋችሁም ምድር እመልሳችኋለሁ።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 በእርግጥ እላችኋለሁ ታገኙኛላችሁ፤ እኔም ወደ ምድራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ እናንተን ከበተንኩበት ከየትኛውም አገርና ከየትኛውም ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ እኔ እናንተን ነቅዬ እንድትሰደዱ ከማድረጌ በፊት ወደ ነበራችሁበት ምድር መልሼ አመጣችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እገለጥላችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፤ ከአሕዛብ ሁሉ ዘንድ እናንተንም ከበተንሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፥ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ካሳደድሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ። Ver Capítulo |