ሰማርያንና የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ከነዘሮቹ እንደ ቀጣሁ ሁሉ ኢየሩሳሌምንም እቀጣለሁ፤ ሳሕን ከተወለወለ በኋላ ተደፍቶ እንደሚቀመጥ፥ እኔም ኢየሩሳሌምን ከኃጢአት አጸዳታለሁ።
ኤርምያስ 44:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ያመጣሁትን ክፉ ነገር ሁሉ ራሳችሁ አይታችኋል፤ እነሆ፥ ዛሬ ባድማ ሆነዋል፥ የሚቀመጥባቸውም የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ያመጣሁትን ታላቅ ጥፋት አይታችኋል፤ ዛሬ ማንም የማይኖርባቸው ባድማ ሆነው ይታያሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በኢየሩሳሌምና በሌሎችም የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ያመጣሁትን ጥፋት እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል፤ አሁንም እንኳ እንደ ፈራረሱ ናቸው፤ ማንም አይኖርባቸውም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ያመጣሁትን ክፉ ነገር ሁሉ አይታችኋል፤ ከክፋታቸውም የተነሣ እነሆ ዛሬ ባድማ ሆነዋል፤ የሚቀመጥባቸውም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ያመጣሁትን ክፉ ነገር ሁሉ አይታችኋል፥ እነሆ፥ ዛሬ ባድማ ሆነዋል፥ የሚቀመጥባቸውም የለም። |
ሰማርያንና የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ከነዘሮቹ እንደ ቀጣሁ ሁሉ ኢየሩሳሌምንም እቀጣለሁ፤ ሳሕን ከተወለወለ በኋላ ተደፍቶ እንደሚቀመጥ፥ እኔም ኢየሩሳሌምን ከኃጢአት አጸዳታለሁ።
እኔም፤ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት፤ እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤ “ከተሞች እስኪፈራርሱና፤ የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፤ ቤቶችም ወና እስኪሆኑና፤ ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤
እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ ይላል ጌታ፥ ወደዚህችም ከተማ እመልሳቸዋለሁ፤ እርሷንም ይወጋሉ ይይዙአታልም በእሳትም ያቃጥሉአታል፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”
አንበሳ ከችፍግ ዱሩ ወጥቶአል፥ አሕዛብንም የሚያጠፋ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ለማድረግ ከስፍራው ወጥቶአል፥ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ይሆናሉ።
ጌታም ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኩሰት መታገሥ አልቻለም፤ ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ መሣቀቂያም መረገሚያም ሆናለች ዛሬም እንደሆነ የሚኖርባት የለም።
ስላጠናችሁ፥ በጌታም ላይ ኃጢአትን ስለ ሠራችሁ፥ የጌታንም ድምፅ ስላልሰማችሁ፥ በሕጉና በሥርዓቱም በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፥ ስለዚህ ዛሬ እንደሆነ ይህ ክፉ ነገር ደርሶባችኋል።”
ምድሪቱም ባድማ ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም አደባባይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የሙሽራውን ድምፅና የሙሽራይቱን ድምፅ አጠፋለሁ።
አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! በአሕዛብ መካከል ታላቅ የነበረች እንደ መበለት ሆናለች፥ በአውራጆች መካከል ልዕልት የነበረች ተገዢ ሆናለች።
ዔ። የሚያጽናናኝ ነፍሴንም የሚያበረታት ከእኔ ርቆአልና ስለዚህ አለቅሳለሁ፥ ዓይኔ፥ ዓይኔ ውኃ ያፈስሳል። ጠላት በርትቶአልና ልጆቼ ጠፍተዋል።
ምድርሪቱም በእነርሱ ትተዋለች፤ ያለ እነርሱም ባድማ ሆና እስከተቀመጠችበት ጊዜ ድረስ ሰንበታትን በማድረግዋ ትደሰታለች፤ ፍርዴንም ስላልተቀበሉ፥ ነፍሳቸውም ሥርዓቴን ስለ ተጸየፈች የበደላቸውን ቅጣት ይቀበላሉ።
ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።
ሙሴም እስራኤላውያንን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ በዐይኖቻችሁ ፊት በግብጽ ምድር፥ በፈርዖን፥ በአገልጋዮቹ ሁሉና በመላ አገሩ ላይ ያደረገውን አይታችኋል።