Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢያሱ 23:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እናንተም ጌታ አምላካችሁ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ ጌታ አምላካችሁ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ሲል በእነዚህ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደረገውን ማንኛውንም ነገር እናንተው ራሳችሁ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋላችሁ ራሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አምላካችን እግዚአብሔር እናንተን ለመርዳት በእነዚህ ሕዝቦች ላይ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ተዋግቶላችኋል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እና​ን​ተም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ስለ እና​ንተ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ስለ እና​ንተ የተ​ዋጋ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እናንተም አምላካቸሁ እግዚአብሔር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፥ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 23:3
13 Referencias Cruzadas  

ጌታ ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ።”


የእስራኤልም አምላክ ጌታ ለእስራኤል ስለ ተዋጋላቸው ኢያሱ እነዚህን ነገሥታት ሁሉ ምድራቸውንም በአንድ ጊዜ ያዘ።


ጌታ ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና ጌታ የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።


ዐይኖቻችሁም ያያሉ፥ እናንተም፦ “ከእስራኤል ዳርቻ ወዲያ ጌታ ታላቅ ይሁን!” ትላላችሁ።


ድልን ያቀዳጃችሁ ዘንድ ስለ እናንተ ጠላቶቻችሁን ሊወጋ አብሮአችሁ የሚወጣው ጌታ እግዚአብሔር ነውና።’


“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።


በዓይናችሁ ፊት በግብጽ እንዳደረገላችሁ ሁሉ፥ በፊታችሁ የሚሄደው ጌታ አምላካችሁ ስለ እናንተ ይዋጋል፤


ጌታ አምላካችሁ እንደ ተናገራችሁ ስለ እናንተ የሚዋጋ እርሱ ነውና ከእናንተ አንዱ ሰው ሺህ ሰውን ያሳድዳል።


እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ ቅጠልማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፥ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቆጣኝን ቁርባናቸውን አቀረቡ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቁርባናቸውን አፈሰሱ።


በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንዴት እንደ ተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።


“በልብህም፦ ‘እነዚህ ሕዝቦች ከእኔ ይበልጣሉ፤ እንዴትስ አድርጌ አስወጣቸዋለሁ?’ ብለህ፥


ነገሥታቶቻቸውንም በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋለህ፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ማንም ተቋቁሞህ በፊት ሊቆም አይችልም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios