La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 36:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም ሆነ፤ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት ይህ ቃል ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ የነበረው ኢዮአቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት እንዲህ የሚል ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ በአራተኛው ዓመት እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ይህ ቃል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም ሆነ፥ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 36:1
9 Referencias Cruzadas  

ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ።


በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።


ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ ልጅ ከኢዮስያስ ከዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሀያ ሦስቱ ዓመታት፥ የጌታ ቃል ወደ እኔ መጣ፥ እኔም ማልጄ ተነሥቼ ተናገርኋችሁ፤ ተናገርሁ፥ ሆኖም ግን አልሰማችሁም።


በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦


እንዲህም ሆነ፤ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር፥ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሁሉ ከይሁዳም ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት ሕዝብ ሁሉ በጌታ ፊት ለመጾም አዋጅ ነገሩ።


በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት የኔርያ ልጅ ባሮክ ኤርምያስ በቃል እየነገረው እነዚህን ቃሎች በመጽሐፍ በጻፋቸው ጊዜ፥ ነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው።


ስለ ግብጽ፤ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ በከርከሚሽ ስለ ነበረው፥ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታው ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ኒካዑ ሠራዊት።