2 ዜና መዋዕል 36:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ኢዮአቄም በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ። በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ኢዮአቄም በይሁዳ ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እርሱም ኃጢአት በመሥራቱ አምላኩን እግዚአብሔርን አሳዘነ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ዘካራ የምትባል የኔሬያሳ ልጅ የራማ ሴት ነበረች፤ አባቶቹም እንዳደረጉ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ። 5 ‘ሀ’ በእነዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደዚያ ሀገር መጣና ሦስት ዓመት ተገዛለት። ከእርሱም ከዳ። 5 ‘ለ’ እግዚአብሔርም የከለዳውያንንና የሶርያውያንን፥ የሞዓባውያንንና የአሞናውያንን ልጆችና የሰማርያን አደጋ ጣዮች ላከበት፤ ከዚህም በኋላ በአገልጋዮቹ በነቢያት እንደ ተነገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ራቁ። 5 ‘ሐ’ ነገር ግን ምናሴ ስለሠራቸው ኀጢአቶችና ኢዮአቄም ስላፈሰሰው ንጹሕ ደም፥ ኢየሩሳሌምንም በንጹሕ ደም ስለ ሞላት ከፊቱ ይርቁ ዘንድ የእግዚአብሔር ቍጣ በይሁዳ ላይ ነበር። 5 ‘መ’ እግዚአብሔርም ሊያጠፋቸው አልፈለገም ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ። Ver Capítulo |