ኤርምያስ 23:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ይላል ጌታ። ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ እንዳላየው፣ በስውር ቦታ ሊሸሸግ የሚችል አለን?” ይላል እግዚአብሔር። “ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን” ይላል እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ሰማይንና ምድርን የሞላሁ አይደለሁምን? ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ እኔ አላየውምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው በስውር ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር። |
“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ!
ነገር ግን ሰማይና ከሰማያት በላይ ያለ ሰማይ እርሱን ለመያዝ አይችልምና ለእርሱ ቤት መሥራት ማን ይችላል? በፊቱ ዕጣን ከማጠን በቀር ቤት ልሠራለት የምችል እኔ ማን ነኝ?
“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ አንተን መያዝ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ ይሆን?
ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።
እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት፥ የመሸሸጊያውንም ስፍራዎች ገለጥሁ፥ እርሱም ለመሸሸግ አይችልም፤ ዘሩም ወንድሞቹም ጎረቤቶቹም ጠፍተዋል እርሱም የለም።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።