Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 23:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 “አለምሁ አለምሁ” እያሉ በስሜ ትንቢትን በሐሰት የሚናገሩትን የነቢያትን ነገር ሰምቻለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “ ‘ሕልም ዐለምሁ ሕልም ዐለምሁ’ እያሉ በስሜ የሐሰት ትንቢት የሚናገሩትን የነቢያትን ቃል ሰምቻለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በስሜ ሐሰት የሚናገሩት ነቢያት የሚሉትን ሰማሁ፤ ‘ሕልም አልሜአለሁ፥ ሕልም ዐልሜአለሁ’ እያሉ ይጮኻሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሕል​ምን አለ​ምን እያሉ በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን የነ​ቢ​ያ​ትን ነገር ሰም​ቻ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አለምሁ አለምሁ እያሉ በስሜ ሐሰትን የሚናገሩትን የነቢያትን ነገር ሰምቻለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 23:25
24 Referencias Cruzadas  

ዮሴፍም ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እነርሱም እንደገና አብዝተው ጠሉት።


ደግሞም ሌላ ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም፦ “እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ፥ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ሲሰግዱልኝ አየሁ።” ሲል ነገራቸው።


አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ፥ ሐሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ።


የዓመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ።


አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የአመንዝራነትሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ፥ በሜዳም አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?”


ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “ነቢያቱ በስሜ የውሸትን ትንቢት ይናገራሉ፤ አላክኋቸውም፥ አላዘዝኋቸውም፥ አልተናገርኋቸውም፤ የውሸትን ራእይ ምዋርትንም ከንቱንም ነገር የልባቸውንም ሽንገላ ይሰብኩላችኋል።


ዓይኔ በመንገዶቻቸው ሁሉ ላይ ነው፤ ከፊቴም አልተሰወሩም፥ ኃጢአታቸውም ከዓይኔ አልተሸሸገም።


የሚያልም ነቢይ ሕልምን ይናገር፤ ቃሌም ያለበት ቃሌን በእውነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው? ይላል ጌታ።


እነሆ፥ ሐሰትን ትንቢት በሚያልሙ በሚናገሩም፥ በሐሰታቸውና በድፍረታቸውም ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ፤ እኔም አልላክኋቸውም አላዘዝኋቸውምም፥ ለእነዚህም ሕዝብ በማናቸውም ነገር አይጠቅሙአቸውም፥ ይላል ጌታ።


ከምድራቸሁ እንድትርቁ፥ እኔም እንዳሳድዳችሁ እናንተም እንድትጠፉ ሐሰተኛ ትንቢትን ይነግሩአችኋልና።


እኔ አልላክኋቸውምና፤ ነገር ግን እኔ እንዳሳድዳችሁ፥ እናንተና ትንቢት የሚነግሩአችሁ ነቢያትም እንድትጠፉ፥ በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገራሉ፥ ይላል ጌታ።”


በእስራኤል ዘንድ አሳፋሪ ነገር አድርገዋልና፤ ከባልንጀሮቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፤ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና፤ እኔም አውቀዋለሁ ምስክርም ነኝ፥ ይላል ጌታ።’ ”


የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ በመካከላችሁ ያሉት ነብዮቻችሁና ምዋርተኞቻችሁ አያታልሉአችሁ፥ እናንተም የምታልሙትን ሕልም አትስሙ።


አደመጥሁ ሰማሁም፤ ቅንን ነገር አልተናገሩም፤ አንድም ሰው፦ ‘ምን አድርጌአለሁ?’ ብሎ ከክፋቱ ንስሐ የገባ የለም፤ ወደ ጦርነትም እንደሚሮጥ ፈረስ እያንዳንዱ በየመንገዱ ይሄዳል።


ኖን። ነቢዮችሽ ከንቱና ሐሰተኛ ራእይ አይተውልሻል፥ ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፥ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል።


ነቢዮችዋ ጌታ ሳይናገር “ጌታ እንዲህ ይላል” እያሉ የሐሰት ራእይ በማየትና በውሸት ሟርት፥ በኖራ ይለቀልቋቸዋል።


ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፥ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ወጣቶቻችሁም ራእይ ያያሉ፥


አሁንም ቢሆን ማንም ትንቢት ቢናገር የወለዱት አባቱና እናቱ፦ “አንተ በጌታ ስም ሐሰትን ተናግረሃልና በሕይወት አትኖርም” ይሉታል። ትንቢትንም ሲናገር የወለዱት አባትና እናቱ ይወጉታል።


እርሱም እንዲህ አለ፦ “እባካችሁ፥ ቃሎቼን ስሙ፤ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር፥ እኔ ጌታ በራእይ እገለጥለታለሁ፥ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ።


እርሱ ይህን ሲያስብ ሳለ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፤ እንዲህም አለው “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርሷ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።


ስለዚህ በጨለማ የተናገራችሁት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይታወጃል።


ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።


በፊቱም የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ እኛ መልስ መስጠት በሚገባን ከእርሱ ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው።


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ፥ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos