ኤርምያስ 21:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት ቤት ሆይ! ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣና ማንም ሳያጠፋው እንዳይነድድ፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፥ የተበዘበዘውንም ከጨቋኙ እጅ አድኑ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳዊት ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ካደረጋችሁት ክፋት የተነሣ፣ ቍጣዬ እንዳይቀጣጠል፣ ማንም ሊያጠፋው እስከማይችል እንዳይነድድ፣ በየማለዳው ፍትሕን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ሰው፣ ከጨቋኙ እጅ አድኑት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊት ቤት ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይነድድና ማንም ሳያጠፋው እንዳያቃጥል፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊት ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣና ማንም ሳያጠፋው እንዳይነድድ፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ። |
ለዳዊት ቤት፤ “ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል” የሚል ወሬ በደረሰ ጊዜ፤ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የአካዝና የሕዝቡ ልብ እንዲሁ ተናወጠ።
አንተም የሰጠሁህን ርስት ትለቅቃለህ፥ በማታውቃትም ምድር ለጠላቶችህ ባርያ እንድትሆን አደርግሃለሁ፤ ለዘለዓለም የሚነድደውን እሳት በቁጣዬ አንድዳችኋልና።”
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸዋልም አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ ስለ ክፉ ሥራችሁ እጐበኛችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።
“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።
ጌታ በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቁጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምናልባት ልመናቸው በጌታ ፊት ይቀርብ ይሆናል፥ ሁሉም ከክፉ መንገዱ ይመለስ ይሆናል።”
እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሆይ! ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለጌታ እራሳችሁን ግረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።”
ጌታም ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኩሰት መታገሥ አልቻለም፤ ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ መሣቀቂያም መረገሚያም ሆናለች ዛሬም እንደሆነ የሚኖርባት የለም።
ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን ቃል ተናግራችኋልና እነሆ፥ በአፍህ ውስጥ ቃሌን እሳት፥ ይህንም ሕዝብ እንጨት አደርጋለሁ፥ ትበላቸዋለችም።
ወፍረዋል ሰብተዋልም፥ ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል፤ የድሀ አደጎች ነገር መልካም እንዲሆንላቸው አልተምዋገቱላቸውም፥ የችግርተኞችንም ፍርድ አልፈረዱላቸውም።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቁጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይወርዳል፤ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።”
በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ አስፈሪ ፍፃሜ ያመጣባቸዋልና።
በውስጧ ያለው ጌታ ጻድቅ ነው፥ ስሕተት አያደርግም፥ ማለዳ ማለዳ ፍርዱን ለብርሃን ይሰጣል፥ አያቋርጥምም፤ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።
ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። ክፉ ብታደርግ ግን ፍራ፤ በከንቱ ሰይፍ አይታጠቅምና፤ ቁጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና።