ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው ቢልዳድ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።
ኢሳይያስ 51:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ሁለት ነገሮች ሆነውብሻል፥ ማንስ ያስተዛዝንሻል? መፈታትና ጥፋት፥ ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እንዴትስ አድርጌ አጽናናሻለሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ በጥፋት ላይ ጥፋት መጥተውብሻል፤ ታዲያ ማን ያጽናናሻል? እነርሱም መፈራረስና ጥፋት፣ ራብና ሰይፍ ናቸው፤ ታዲያ ማን ያስተዛዝንሽ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውድመትና ጥፋት፥ ራብና ጦርነት፥ እነዚህ ሁለት ነገሮች ደርሰውብሻል፤ የሐዘንሽ ተካፋይ የሚሆን ማነው? ማንስ ያጽናናሻል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እነዚህ ሁለቱ ይጠብቁሻል፤ ማን ያስተዛዝንሻል? እነርሱም ጥፋትና ውድቀት ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እንግዲህ የሚያጽናናሽ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ ሁለት ነገሮች ሆነውብሻል፥ ማንስ ያስተዛዝንሻል? መፈታትና ጥፋት ራብና ሰይፍ ናቸው፥ እንዴትስ አድርጌ አጽናናሻለሁ? |
ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው ቢልዳድ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።
ወንድሞቹና እኅቶቹ ቀድሞም ያውቁት የነበሩት ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤቱም ከእርሱ ጋር እንጀራ በሉ፥ ስለ እርሱም አዘኑለት፥ ጌታም ካመጣበት ክፉ ነገር ሁሉ አጽናኑት፥ እያንዳንዳቸውም ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት።
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ፥ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፥ በሚገፉአቸውም እጅ ኃይል ነበረ፥ እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።
አሁን ግን እነዚህ ሁለት ነገሮች፥ የወላድ መካንነትና መበለትነት፥ በአንድ ቀን በድንገት ይመጡብሻል፤ ምንም መተት ብታበዥና ምንም ዓይነት አስማት ቢኖርሽም ፈጽሞ አይቀሩልሽም።
ምናሴ ኤፍሬምን፤ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤ በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
ላሜድ። እናንተ መንገድ አላፊዎች ሁሉ፥ በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቁጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደተደረገው እንደ እኔ መከራ የሚመስል መከራ እንዳለ ተመልከቱ፥ እዩ።
ጤት። አደፍዋ በልብስዋ ዘርፍ ነበረ፥ ፍጻሜዋን አላሰበችም፥ ስለዚህ በድንቅ ተዋርዳለች፥ የሚያጽናናትም የለም፥ አቤቱ፥ ጠላት ከፍ ከፍ ብሏልና መከራዬን ተመልከት።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን ሰይፍ፥ ራብ፥ ክፉ አውሬና ቸነፈር፥ ሰውንና እንስሳን ከእርሷ ለማጥፋት ብሰድድም፥
የምድሩንም እጽዋት በልተው ከጨረሱ በኋላ፥ እኔ፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ታናሽ ነውና እንዴት ይቆማል?” አልሁ።