አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ፥ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፥ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”
ኢሳይያስ 49:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፥ ጌታ፥ ሰዎች በሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው፥ ለገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ታማኙ ስለ ጌታ ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር፣ ታዳጊ የሆነው የእስራኤል ቅዱስ፣ ለተናቀውና በሕዝብ ለተጠላው፣ የገዦች አገልጋይ እንዲህ ይላል፤ “ነገሥታት አይተውህ ይነሣሉ፤ ልዑላንም አይተው ይሰግዳሉ፤ ምክንያቱም የመረጠህ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ታማኝ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕዝቦች ዘንድ በጣም ለተናቅህና ለተጠላህ፥ ለገዢዎችም አገልጋይ ለሆንክ ለአንተ፥ አዳኙ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ነገሥታት ሲያዩህ ይነሡልሃል፤ ልዑላንም ይሰግዱልሃል፤ ይህም የሚሆነው በመረጠህ በታማኙ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ምክንያት ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፥ እግዚአብሔር፥ ሰዎች በሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው ለገዢዎች ባሪያ እንዲህ ይላል፦ ስለ ታማኙ ስለ እግዚአብሔር ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ። |
አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ፥ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፥ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”
በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥ በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን መንጋ ገሥጽ፥ እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ፥ ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው።
ጌታ ግን ያዕቆብን ይምረዋል፥ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፥ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፤ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፥ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይተሳሰራል።
በዚያም ቀን ጌታ ለግብጻዊያን ራሱን ይገልጣል፤ ግብጻውያንም ጌታን ያውቃሉ፤ በመሥዋዕትና በእህል ቁርባንም ያመልኩታል፤ ለጌታም ስእለት ይሳላሉ፤ የተሳሉትንም ይፈጽማሉ።
በዚያ ቀን ከግብጽ ወደ አሦር መንገድ ይዘረጋል፤ አሦራዊያንም ወደ ግብጽ፥ ግብፃዊውም ወደ አሦር ይሄዳሉ፤ ግብፃውያንም ከአሦራውያን ጋር ይሰግዳሉ።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለጌታ ይሰግዳሉ።
ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፥ እቴጌዎቻቸውም ሞግዝቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።
አስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን አስበላቸዋለሁ፥ እንደ ጣፋጭም ወይን ጠጅ ደማቸውን ጠጥተው ይሠክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ ጌታ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ፥ የያዕቆብ ኃያል እንደሆንሁ ያውቃል።
ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር። መኰንኖቹም “ሌሎችን አዳነ፤ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠው ክርስቶስ ከሆነ፥ ራሱን ያድን፤” እያሉ ያፌዙበት ነበር።
እነርሱ ግን “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “ንጉሣችሁን ልስቀለውን?” አላቸው። የካህናት አለቆችም “ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም” ብለው መለሱለት
የካህናት አለቆችና ሎሌዎችም ባዩት ጊዜ “ስቀለው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “እኔስ አንዲት በደል እንኳን አላገኘሁበትምና እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት” አላቸው።
አንተም ጌታ አምላካችሁ እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ፥ ለሚወዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደሆነ እወቅ፤
ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”
“በፊላደልፊያም ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ ‘ቅዱስና እውነተኛ የሆነው፥ የዳዊትም መክፈቻ ያለው፥ ሲከፍትም፥ ማንም የማይዘጋው፤ ሲዘጋም ማንም የማይከፍተው፤ እርሱ እንዲህ ይላል’፦