ዮሐንስ 18:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 ሁሉም በድጋሚ “በርባንን እንጂ ይህን ሰው አይደለም” እያሉ ጮኹ። በርባን ግን ወንበዴ ነበረ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም40 እነርሱም እንደ ገና በመጮኽ፣ “የለም፤ እርሱን አይደለም! በርባንን ፍታልን!” አሉ። በርባን ግን ወንበዴ ነበረ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 እነርሱ ግን “በርባንን ፍታልን እንጂ ይህን አይደለም!” እያሉ ጮኹ። በርባን ግን ወንበዴ ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 ዳግመኛም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፥ “በርባንን እንጂ ይህን አይደለም፤” አሉ፤ በርባን ግን ወንበዴ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 ሁሉም ደግመው፦ በርባንን እንጂ ይህን አይደለም እያሉ ጮኹ። በርባን ግን ወንበዴ ነበረ። Ver Capítulo |