ኢሳይያስ 47:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወፍጮ ወስደሽ ዱቄትን ፍጪ፤ መሸፈኛሽን አውጪ ረጅሙንም ልብስሽን አውልቀሽ ጣይው፤ ባትሽን ግለጪ፥ ወንዙን ተሻገሪ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወፍጮ ወስደሽ እህል ፍጪ፤ መሸፋፈኛሽን አውልቂ፤ ቀሚስሽንም ከፍ ከፍ አድርጊ፤ ባትሽን ግለጪ፤ እየተንገዳገድሽ ወንዙን ተሻገሪ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ መጅ አንሥተሽ ዱቄት ፍጪ፤ ዐይነ ርግብሽን ግለጪ፤ ካባሽን አውልቂ፤ ቀሚስሽን ከፍ አድርገሽ በተራቈተ ቅልጥም ወንዙን ተሻገሪ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወፍጮ ወስደሽ ዱቄትን ፍጪ፤ ክንብንብሽን ግለጪ፤ ሽበትሽ ይታይ፤ ባትሽን ግለጪ፤ ወንዙንም ተሻገሪ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወፍጮ ወስደሽ ዱቄትን ፍጪ፥ መሸፈኛሽን አውጪ ረጅሙንም ልብስሽን አውልቀሽ ጣይው፥ ባትሽን ግለጪ፥ ወንዙን ተሻገሪ። |
በግብጽም ምድር ያለ በኩር ሁሉ፥ በዙፋኑ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኩር ጀምሮ በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ ባርያይቱ በኩር ድረስ፥ የከብቱም በኩር ሁሉ ይሞታል።
እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጉስቁልና ይነዳቸዋል።
እናንተ ዓለመኛ ሴቶች ሆይ፥ በፍርሃት ራዱ፤ ተማምናችሁ የምትቀመጡ፥ ተንቀጥቀጡ፤ ልብሳችሁን አውልቁ፥ ዕራቁታችሁን ሁኑ፥ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ።
በራሱ ምድር ላይ መውደቅያው እስከሚመጣ ጊዜ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁም ለልጅ ልጁም ያገለግላሉ፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እርሱን አገልጋይ ያደርጉታል።
በሻፊር የምትቀመጪ ሆይ፥ በራቁትነትና በእፍረት እለፊ፤ በጻኣናን የምትቀመጠው አልወጣችም፤ የቤትሐኤጼል ለቅሶ የመቆሚያ ስፍራውን ከእናንተ ይወስዳል።
ከዚያም ፍልስጥኤማውያን ያዙት፤ ዐይኖቹን አውጥተው ወደ ጋዛ ይዘውት ወረዱ፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም እስር ቤት ውስጥ እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤