ኢሳይያስ 33:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገለባን ትጸንሳላችሁ፥ ዕብቅንም ትወልዳላችሁ፤ እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገለባን ፀነሳችሁ፤ እብቅንም ወለዳችሁ፤ እስትንፋሳችሁም የሚበላችሁ እሳት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገለባን ፀንሳ እብቅ እንደምትወልድ እስትንፋሳችሁ እንደ እሳት ሆኖ ያጋያችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬ ታያላችሁ፤ ዛሬ ታደንቃላችሁ፤ የመንፈሳችሁም ኀይል ከንቱ ይሆናል፤ እሳትም ትበላችኋለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገለባን ትጸንሳላችሁ፥ ዕብቅንም ትወልዳላችሁ፥ እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት። |
ሕዝቦች እንደ ብዙ ውኃ ጩኸት ይጮኻሉ፤ እርሱ ግን ይገሥጻቸዋል፤ እነርሱም እየሸሹ ይርቃሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ በነፋስ ፊት፥ ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረውም ትቢያ ይበተናሉ።
ስለዚህ የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፤ ድርቆሽም በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ፤ የእነርሱም ሥር እንዲሁ ይበሰብሳል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋልና፤ የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል አቃለዋል።
እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾህንና ኩርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነዳል፤ ጢሱም ተትጐልጉሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።
ሳትሸጠው የአንተ አልነበረምን? ከሸጥኸውስ በኋላ በሥልጣንህ አልነበረምን? ይህን ነገር ስለምን በልብህ አሰብህ? እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም፤” አለው።