ኢሳይያስ 23:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፤ በግብጽ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፣ በግብጽ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጢሮስ መደምሰስዋን በሰሙ ጊዜ ግብጻውያን በድንጋጤ ይታወካሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወሬዋ ወደ ግብፅ በደረሰ ጊዜ ስለ ጢሮስ ምጥ ይይዛቸዋል። |
ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለመደምሰስ የተረፉትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና ለማጥፋት ስለሚመጣው ቀን ነው፤ ጌታ ፍልስጥኤማውያንና የከፍቶርን ደሴት ትሩፍ ያጠፋልና።
በዚያ ቀን ያለ ስጋት የተቀመጠችውን ኢትዮጵያን ለማስፈራራት መልእክተኞች ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ፤ እንደ ግብጽም ቀን ጭንቀት ይሆንባቸዋል፤ እነሆ መጥቷልና።