ኢሳይያስ 22:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ በአስተማማኝ ስፍራ የተተከለው ችንካር ይወልቃል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፤ በእርሱም ላይ የተንጠለጠለው ሸክም ይጠፋል፤ ይህን ጌታ ተናግሮአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ቀን” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ “በአስተማማኝ ስፍራ የተተከለ ካስማ ይነቀላል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፤ በርሱም ላይ የተንጠለጠለው ሸክም ወድቆ ይከሰከሳል፤” እግዚአብሔር ይህን ተናግሯልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ቀን የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህ ሁሉ ነገር በሚፈጸምበት ጊዜ ግን ጠንካራው የዕቃ መስቀያ ኲላብ ተነቅሎ ይወድቃል፤ በኲላቡም ላይ ተሰቅሎ የነበረው ዕቃ ሁሉ ተሰባብሮ ይወድቃል።’ ” ይህን የተናገረ እግዚአብሔር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ በታመነው ስፍራ የተተከለው ችንካር ይወልቃል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፤ በእርሱም ላይ የተሰቀለው ሸክም ይጠፋል፤” እግዚአብሔር እንዲህ ተናግሮአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ በታመነው ስፍራ የተተከለው ችንካር ይወልቃል፥ ተሰብሮም ይወድቃል፥ በእርሱም ላይ የተሰቀለው ሸክም ይጠፋል፥ እግዚአብሔር ተናግሮአል። |
የአባቱንም ቤት ክብር ሁሉ ልጆቹንም የልጅ ልጆቹንም፥ እያንዳንዷን ትንንሽ ዕቃ፥ ከሲኒ ጀምሮ እስከ ጋን ድረስ ያለ የቤት ዕቃ ሁሉ በርሱ ላይ ይንጠለጠላል።
ንዴቴ ያልፋል፥ ቁጣዬም በእነርሱ ላይ እንዲያርፍ አደርጋለሁ፥ እጽናናለሁም፥ ቁጣዬን በእነርሱ ላይ በፈጸምሁ ጊዜ እኔ ጌታ በቅንዓቴ እንደ ተናገርሁ ያውቃሉ።
በአንቺ ላይ በንዴትና በቁጣ፥ በመዓትም ዘለፋ ፍርድን ባደረግሁብሽ ጊዜ፥ በዙሪያሽ ላሉ አገሮች መሰደቢያና መተረቻ፥ ማስጠንቀቂያና ድንጋጤ ትሆኛለሽ፥ እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።
ራብንና ክፉዎችን አራዊት እሰድድባችኋለሁ፥ ልጆችሽን ያሳጡሻል፥ ቸነፈርና ደምም በአንቺ በኩል ያልፋሉ፥ ሰይፍንም አመጣብሻለሁ። እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።