ኢሳይያስ 18:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንት በዓለም ውስጥ ያላችሁና በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሆይ፥ ምልክት በተራሮች ላይ በሚወጣ ጊዜ ተመልከቱ! መለከትም በተነፋ ጊዜ ስሙ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የዓለም ሕዝቦች፣ በምድርም የምትኖሩ ሁሉ፣ በተራሮች ላይ ምልክት ሲሰቀል ታዩታላችሁ፤ መለከትም ሲነፋ ትሰሙታላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድር የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ! በተራሮች ጫፍ ላይ የተተከለ የሰንደቅ ዓላማ ምልክት ሲውለበለብ አስተውሉ! መለከት ሲነፋ ስሙ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየሀገራቸው ይቀመጣሉ፤ ከተራሮች ራሶችም እንደ ዓላማ ይይዙታል፤ እንደ መለከት ድምፅም ይሰማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓለም የምትኖሩ ሁሉና በምድር የምትቀመጡ ሆይ፥ ምልክት በተራሮች ላይ በተነሣ ጊዜ እዩ፥ መለከትም በተነፋ ጊዜ ስሙ። |
ለመንግሥታት ምልክትን ያቆማል፤ ከእስራኤልም የተሰደዱትን መልሶ ያመጣቸዋል፤ የተበተኑትን የይሁዳ ሕዝብ፤ ከአራቱ የምድር ማእዘን ይሰበስባል።
በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፤ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ! በመንግሥታትም መካከል፤ እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊቱን ለጦርነት አሰልፎአል።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፥ ዓላማዬንም ወደ ወገኖች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም በዕቅፋቸው ያመጡአቸዋል፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል።
በምድር ላይ ዓላማን አንሡ በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ፥ አሕዛብንም ለጦርነት በእርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ጥሩባት አለቃንም በእርሷ ላይ ሹሙ፤ እንደ ጠጉራም ኩብኩባ ፈረሶችን በእርሷ ላይ አውጡ።
ጌታም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ የአምላኩም ቀስት እንደ መብረቅ ይወጣል፤ እግዚአብሔር ጌታም መለከትን ይነፋል፥ ከደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይመጣል።