ኢሳይያስ 13:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፤ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ! በመንግሥታትም መካከል፤ እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊቱን ለጦርነት አሰልፎአል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ፤ በመንግሥታትም መካከል፣ እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ! የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሰራዊቱን ለጦርነት አሰልፏል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 በተራሮች ላይ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ፤ ይህም ጩኸት በአንድነት የተሰበሰቡ የብዙ ሕዝብ መንግሥታት ሁካታ ነው፤ የሠራዊት አምላክ ሠራዊቱን ለጦርነት እያዘጋጀ ነው፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ። የተሰበሰቡ ነገሥታትና የአሕዛብ ድምፅም አለ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ተዋጊዎች አሕዛብ ይመጡ ዘንድ አዘዘ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ። የተከማቹት የአሕዛብ መንግሥታት የውካታ ጫጫታ አለ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊትን ለሰልፍ አሰልፎአል። Ver Capítulo |