ኢሳይያስ 13:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መዓት፤ ቁጣው በሚነድበት ቀን፤ ሰማያትን እነቀንቃለሁ፤ ምድርንም ከስፍራዋ አናውጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት፣ ቍጣው በሚነድድበት ቀን፣ ሰማያትን እነቀንቃለሁ፤ ምድርንም ከስፍራዋ አናውጣለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የሠራዊት አምላክ ቊጣዬን በምገልጥበት ጊዜ ሰማይን አንቀጠቅጣለሁ፤ ምድርም ከስፍራዋ እንድትናወጥ አደርጋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት በጽኑ ቍጣው ቀንም ሰማያት ይንቀጠቀጣሉ፤ ምድርም ከመሠረቷ ትናወጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት በጽኑ ቍጣ ቀንም ሰማያትን አነቃንቃለሁ፥ ምድርም ከስፍራዋ ትናወጣለች። |
የሰማይም ሠራዊት ሁሉ ይሟሽሻሉ፤ ሰማያትም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ፤ ሠራዊታቸው ሁሉ ከወይንና ከበለስ ላይ እንደሚረግፍ ቅጠል ይረግፋል።
አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ ከዚህ በኋላ ቅንጡና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።
ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንሡ፥ ወደ ታችም ወደ ምድር ተመልከቱ፤ ሰማያትን እንደ ጢስ በንነው ይጠፋሉ፥ ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፥ የሚኖሩባትም እንዲሁ ይሞታሉ፤ ማዳኔ ግን ለዘለዓለም ይሆናል፥ ጽድቄም አይፈርስም።
በቀኝ በኩል ይጐርሳሉ፤ ነገር ግን ራባቸው አይታገሥም፤ በግራም በኩል ይበላሉ፤ ነገር ግን አይጠግቡም፤ እያንዳንዱም የገዛ ወገኑን ሥጋ ይበላል።
ላሜድ። እናንተ መንገድ አላፊዎች ሁሉ፥ በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቁጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደተደረገው እንደ እኔ መከራ የሚመስል መከራ እንዳለ ተመልከቱ፥ እዩ።
ጌታም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ያሰማል፥ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፥ ጌታ ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፥ ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።
“ከነዚያ ቀናት መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይሎችም ይናወጣሉ።
የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ በድንገት ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ ምድርም በእርሷም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።