ኢሳይያስ 1:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እምቢ ብላችሁ ብታምፁ ግን ሰይፍ ይበላችኋል።” የጌታ አፍ ይህን ተናግሮአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንቢ ብላችሁ ብታምፁ ግን ሰይፍ ይበላችኋል።” የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሯልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እምቢ ብትሉኝና ብታምፁ ግን ሰይፍ ይበላችኋል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ራሴ እግዚአብሔር ነኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችኋለች፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። |
በዚያን ጊዜ በጌታ ደስ ይልሃል፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፥ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ ይህን የጌታ አፍ ተናግሮአልና።
እድላችሁን ለሰይፍ አደርገዋለሁ፥ ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ፤ በፊቴም ክፉ ነገርን አደረጋችሁ፥ ያልወደድሁትንም መረጣችሁ እንጂ በጠራኋችሁ ጊዜ አልመለሳችሁልኝም፤ በተናገርኩም ጊዜ አልሰማችሁኝም።
ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፥ አትጠፋምም።’ ”
በግብጽ አውጁ፥ በሚግዶልም አሰሙ፥ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ እናንተም፦ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና ተነሥ ራስህንም አዘጋጅ በሉ።
የቃል ኪዳኑንም በቀል የሚበቀል ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተሞቻችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ በመካከላችሁም ቸነፈርን እልክባችኋለሁ፤ በጠላትም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ።
ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?