Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 34:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በጌታ መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም፤ የጌታ አፍ አዝዞአልና፥ መንፈሱ ሰብስቦአቸዋልና ከእነዚህ አንዲት አትጠፋም፥ ጥንዱን የሚያጣ የለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በእግዚአብሔር መጽሐፍ እንዲህ የሚለውን ተመልከቱ፤ አንብቡም፤ ከእነዚህ አንዱ አይጐድልም፤ እያንዳንዷም አጣማጇን አታጣም፤ ይህ ትእዛዝ ከአፉ ወጥቷል፤ መንፈሱ በአንድ ላይ ይሰበስባቸዋልና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስለ ሕያዋን ፍጥረት ሁሉ በእግዚአብሔር መጽሐፍ የተጻፈውን ፈልጋችሁ አንብቡ፤ ከእነዚህ ፍጥረቶች አንዱ እንኳ አይጠፋም፤ የኑሮ ጓደኛ አጥቶ ብቻውን የሚኖርም አይገኝም፤ እግዚአብሔር ራሱ ይህ እንዲሆን ስላዘዘ እርሱ ራሱ በኅብረት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በየ​ቍ​ጥ​ራ​ቸው ያል​ፋሉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ አይ​ጠ​ፋም፤ እርስ በር​ሳ​ቸው አይ​ተ​ጣ​ጡም፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዝ​ዞ​አ​ቸ​ዋ​ልና መን​ፈ​ሱም ሰብ​ስ​ቦ​አ​ቸ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም፥ አፌ አዝዞአልና፥ መንፈሱ ሰብስቦአቸዋልና ከእነዚህ አንዲት አትጠፋም፥ ባልንጀራውንም የሚያጣ የለም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 34:16
22 Referencias Cruzadas  

እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፥ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።


የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአንደበትህ አይለይ፥ ነገር ግን በእርሱ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ እንድትጠብቅና እንድታደርገው በቀንም በሌሊትም አሰላስለው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቃናልሃል ይከናወንልሃልም።


እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ከሕግ አንዲት ኢዮታ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም።


በጌታ ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ በአፉም እስትንፋስ ሠራዊታቸው ተፈጠረ፥


አሁንም ሂድ፥ ለሚመጣውም ዘመን ለዘለዓለም እንዲሆን በሰሌዳ ላይ በመጽሐፍም ውስጥ ጻፍላቸው።


መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥


ልብህን ለምክር ስጥ፥ ጆሮህንም እንዲሁ ለእውቀት ቃላት።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።


በዚያን ጊዜ ጌታን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፤ ጌታም አደመጠ፥ ሰማም፥ ጌታን ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያከብሩ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።


በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባርያዎቹ ለነቢያት ሳይገልጥ ምንም ነገር አያደርግም።


በዚያን ጊዜ በጌታ ደስ ይልሃል፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፥ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ ይህን የጌታ አፍ ተናግሮአልና።


ደግሞም ይህን የበለጠ የሚያረጋግጥ የነቢያት ቃል አለ፤ ጎሕ እስኪቀድ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪገለጥ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚያስተውል ቃሉን ልብ በማለት መልካም ታደርጋላችሁ።


እምቢ ብላችሁ ብታምፁ ግን ሰይፍ ይበላችኋል።” የጌታ አፍ ይህን ተናግሮአልና።


እነሆ፥ እኔ ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት፥ በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፥ በምድር ያለ ሁሉ ይጠፋል።


እናንተ መጻሕፍትን ትመረምራላችሁ፤ በእነርሱም የዘለዓለም ሕይወት እንዳላችሁ ታስባላችሁና፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤


ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ይህ መዝሙር ምስክር ይሆንባቸዋል። በዘራቸው የሚረሳ አይደለምና። ወደ ማልሁላቸው ምድር ሳላስገ ባቸው በፊት ምን ለማድረግ እንደሚያስቡ እንኳን አስቀድሜ ዐውቃለሁ።”


አንተ በር ሆይ፥ ወዮ በል፥ አንቺም ከተማ ሆይ፥ ጩኺ፤ ፍልስጥኤም ሆይ፥ ሁላችሁም ቀልጣችኋል፤ ጢስ ከሰሜን ይመጣል ከጭፍራውም ተለይቶ የሚቀር የለም።


ከዚያም የጌታ ክብር ይገለጣል፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የጌታ አፍ ይህን ተናግሮአል።”


ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በኃይሉ ብዛትና በክህሎቱ ብርታት አንድ እንኳ አይጎለውም።


ከቀስተኞች ቍጥር የቀሩት፥ የቄዳር ልጆች ኃያላን፥ ያንሳሉ፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ ተናግሮአል።


እርሱም መልሶ፦ “ለዘሩባቤል የተባለው የጌታ ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios