ሆሴዕ 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤፍሬምም ክብር እንደ ወፍ በርሮ ይጠፋል፤ መውለድና መፅነስ ማርገዝም አይሆንላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በርሮ ይጠፋል፤ መውለድ፣ ማርገዝና መፀነስ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ታላቅነት እንደ ወፍ በሮ ይጠፋል፤ ከእንግዲህ ወዲህ መፅነስ የለም፤ ማርገዝ የለም፤ መውለድም የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤፍሬምም እንደ ወፍ በረረ፤ ክብራቸው ከመፅነስና ከመውለድ፥ ከማማጥም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤፍሬምም ክብር እንደ ወፍ በርሮ ይጠፋል፥ መውለድና መፅነስ ማርገዝም አይሆንላቸውም። |
ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ነገር ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ዳርቻቸውን ለማስፋት ሲሉ የገለዓድን እርጉዞች ቀድደዋልና ስለ ሦስት የአሞን ልጆች ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።
ከማሕፀኗ የወጣውን እንግዴ ልጅንና የምትወልዳቸውን ልጆች ትጠየፋለች፤ ይህን የምታደርገውም በመከራው ወቅት ጠላቶችህ ከተሞችህን ከበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ እነርሱን ተደብቃ ለመብላት ስትል ነው።
ለላሞች በኩር ግርማ ይሆናል፥ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፥ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፥ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።”