ሆሴዕ 12:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፤ ይሁዳ ግን እስካሁንም ከጌታ ጋር ይመላለሳል ለቅዱሱም ታማኝ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤፍሬም የነፋስ እረኛ ነው፤ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋራ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ የወይራ ዘይትንም ወደ ግብጽ ይልካል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል ሕዝብ ነፋስን ለመጨበጥ በመሞከርና ቀኑን ሙሉ የምሥራቅ ነፋስን ሲያሳድዱ በመዋል ከንቱ ሆነዋል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛሉ፤ ከአሦር ጋር ይዋዋላሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የወይራ ዘይትን ወደ ግብጽ ይልካሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤል ቤትና ይሁዳም በተንኰል ከበቡኝ፤ አሁንም እግዚአብሔር ዐወቃቸው፤ ለእግዚአብሔርም ቅዱስ ሕዝብ ተባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፥ ይሁዳም ከታመነው ቅዱሱ ከእግዚአብሔር ጋር አይጸናም። |
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር እስራኤልን ወረረ፤ ምናሔም በአገሩ መንግሥት ላይ ሥልጣኑን እንዲያጸናለትና እንዲደግፈው ለመማጠን ሠላሳ አራት ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር እጅ መንሻ አድርጎ ለቲግላት ፐሌሴር ሰጠው።
ዳግምም በይሁዳ ተራሮች ላይ በከፍታ ላይ የሚገኙ የማምለኪያ ሥፍራዎችን ሠራ፥ በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን እንዲያመነዝሩ አደረጋቸው፥ ይሁዳንም አሳተው።
እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥ በመካከልህም ቅዱሱ ነኝና የቁጣዬን መቅሠፍት አላደርግም፥ ኤፍሬምንም ዳግመኛ አላጠፋም፤ በመዓትም አልመጣም።
አንተ ብታመነዝር እንኳ እስራኤል ሆይ! ይሁዳ በደለኛ አይሁን፤ እናንተም ወደ ጌልገላ አትግቡ፥ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ፥ ወይም፦ “በሕያው ጌታ እምላለሁ!” ብላችሁም አትማሉ።
ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ወደ ታላቁም ንጉሥ መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ሊፈውሳችሁ፥ ከቁስላችሁም ሊያድናችሁ አልቻለም።
በሐሰት አድርገዋልና፥ ሌባም ገብቶአልና፥ በገላጣም ስፍራ ወንበዴ ቀምቶአልና፤ እስራኤልን በፈወስሁ ጊዜ የኤፍሬም ኃጢአትና የሰማርያ ክፋት ተገለጠ።