ዘፍጥረት 34:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወጣቱም ልጅ፥ የያዕቆብን ልጅ ወድዶአልና፥ ያሉትን ያደርግ ዘንድ አልዘገየም። እርሱም በአባቱ ቤት ካሉት ሁሉ የከበረ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአባቱ ቤተ ሰብ ሁሉ እጅግ የተከበረው ይህ ወጣት የያዕቆብን ልጅ እጅግ ወድዷት ስለ ነበር፣ ያሉትን ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴኬም፥ የያዕቆብን ልጅ እጅግ ወዶአት ስለ ነበር የተነገረውን ሁሉ ለማድረግ ምንም ጊዜ አልወሰደበትም፤ ከዚህም በላይ በቤተሰቡ ውስጥ እጅግ የተከበረ በመሆኑ የፈለገውን ለማድረግ መብት ነበረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናውም ይህን ነገር ያደርግ ዘንድ አልዘገየም፤ የያዕቆብን ልጅ ወድዶአልና፤ እርሱም ከአባቱ ቤተ ሰብእ ሁሉ የከበረ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናውም ያሉትን ያደርግ ዘንድ አልዘገየም የያዕቆብን ልጅ ወደዶአልና እርሱም በአባቱ ቤት ካሉት ሁሉ የከበረ ነበረ። |
እግዚአብሔር በንዕማን አማካይነት ለሶርያ ሠራዊት ድልን ስለ አጐናጸፈ፥ የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ እጅግ የተከበረና የተወደደ ባለሟል ነበር፤ ታዲያ ንዕማን ጀግና ወታደር ሆኖ ሳለ፥ በቆዳ በሽታ ይሠቃይ ነበር።
እንደ ማኅተም በልብህ፥ እንደ ማኅተም በክንድህ አኑረኝ፥ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፥ ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው።
ከእንግዲህ ወዲህ፦ የተተወች አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፦ ውድማ አትባልም፤ ነገር ግን ጌታ ደስታዬ ባንቺ ነው ብሏታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፦ ደስታዬ የሚኖርባት ትባያለሽ ምድርሽም፦ ባል ያገባች ትባላለች።
አይሁድ ግን የሚያመልኩትን የከበሩትንም ሴቶችና የከተማውን መኳንንት አወኩ፤ በጳውሎስና በበርናባስም ላይ ስደትን አስነሥተው ከአገራቸው አወጡአቸው።
አቢሜሌክም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “የንጉሥ ዐማች፥ የክብር ዘቦችህ አዛዥና በቤተሰብህ ዘንድ እጅግ የተከበረው ዳዊትን የመሰለ ታማኝ ከአገልጋዮችህ ሁሉ ማን አለ?