Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 17:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ስለዚህም ከእነርሱ ብዙ፥ ከግሪኮችም የከበሩት ሴቶችና ወንዶች ጥቂት ያይደሉ አመኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ስለዚህ ከእነርሱ ብዙዎቹ አመኑ፤ ደግሞም ከእነርሱ ጋራ ቍጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ዕውቅ የግሪክ ሴቶችና ወንዶችም አመኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ስለዚህ ከእነርሱ ብዙዎች አመኑ፤ ብዙዎች የግሪክ ሀብታሞች ሴቶችና ብዙዎች ግሪካውያን ወንዶችም አመኑ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ያመኑ ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ወገን የሆኑ ብዙ ደጋግ ሴቶ​ችም ነበሩ፤ ወን​ዶ​ችም ብዙ​ዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ስለዚህም ከእነርሱ ብዙ፥ ከግሪኮችም የከበሩት ሴቶችና ወንዶች ጥቂት ያይደሉ፥ አመኑ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 17:12
13 Referencias Cruzadas  

የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ስለዚህ “አንተ የምታንቀላፋ ንቃ፤ ከሙታንም ተነሣ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል፤” ተብሏል።


አይሁድ ግን የሚያመልኩትን የከበሩትንም ሴቶችና የከተማውን መኳንንት አወኩ፤ በጳውሎስና በበርናባስም ላይ ስደትን አስነሥተው ከአገራቸው አወጡአቸው።


ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው መመዘኛ ብዙዎች ጥበበኞች አልነበሩም፥ ብዙዎች ኀያላን አልነበሩም፥ ብዙዎች ታላላቅ ሰዎች አልነበሩም።


በኢቆንዮንም እንደ ቀድሞ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገብተው ከአይሁድና ከግሪክ ሰዎች ብዙ እስኪያምኑ ድረስ ተናገሩ።


ስለዚህ ርኩሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።


ሀብታምም እንደ ሣር አበባ ስለሚረግፍ በውርደቱ ይመካ።


ጳውሎስና በርናባስም ገልጠው “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ ይነገር ዘንድ ያስፈልጋል፤ ከገፋችሁትና የዘለዓለም ሕይወት እንዳይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን፥ እነሆ፥ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን።


ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር እንደሆነ ወይንም እኔ ከራሴ የምናገር እንደሆነ ያውቃል።


የተከበረ የሸንጎ አባልና የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ በድፍረት ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።


እግዚአብሔርም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios