Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 34:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሴኬም፥ የያዕቆብን ልጅ እጅግ ወዶአት ስለ ነበር የተነገረውን ሁሉ ለማድረግ ምንም ጊዜ አልወሰደበትም፤ ከዚህም በላይ በቤተሰቡ ውስጥ እጅግ የተከበረ በመሆኑ የፈለገውን ለማድረግ መብት ነበረው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከአባቱ ቤተ ሰብ ሁሉ እጅግ የተከበረው ይህ ወጣት የያዕቆብን ልጅ እጅግ ወድዷት ስለ ነበር፣ ያሉትን ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ወጣቱም ልጅ፥ የያዕቆብን ልጅ ወድዶአልና፥ ያሉትን ያደርግ ዘንድ አልዘገየም። እርሱም በአባቱ ቤት ካሉት ሁሉ የከበረ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ብላ​ቴ​ና​ውም ይህን ነገር ያደ​ርግ ዘንድ አል​ዘ​ገ​የም፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጅ ወድ​ዶ​አ​ልና፤ እር​ሱም ከአ​ባቱ ቤተ ሰብእ ሁሉ የከ​በረ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ብላቴናውም ያሉትን ያደርግ ዘንድ አልዘገየም የያዕቆብን ልጅ ወደዶአልና እርሱም በአባቱ ቤት ካሉት ሁሉ የከበረ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 34:19
15 Referencias Cruzadas  

ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለ ነበር የቈየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው።


ይህም አባባል ለሐሞርና ለልጁ ለሴኬም መልካም መስሎ ታያቸው፤


ስለዚህ ሐሞርና ልጁ ሴኬም በከተማው በር አጠገብ ወዳለው መሰብሰቢያ ቦታ ሄዱ፤ ለከተማይቱ ነዋሪዎች እንዲህ በማለት ንግግር አደረጉ፤


የከሱትና አስከፊ የሆኑት ላሞች በመጀመሪያ የወጡትን ሰባት የወፈሩ ላሞች ዋጡአቸው።


እግዚአብሔር በንዕማን አማካይነት ለሶርያ ሠራዊት ድልን ስለ አጐናጸፈ፥ የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ እጅግ የተከበረና የተወደደ ባለሟል ነበር፤ ታዲያ ንዕማን ጀግና ወታደር ሆኖ ሳለ፥ በቈዳ በሽታ ይሠቃይ ነበር።


ከቤተሰቡ መካከል እጅግ የተከበረ ያዕቤጽ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እናቱ እርሱን በወለደች ጊዜ ከባድ የምጥ ጣር ደርሶባት ስለ ነበር “ያዕቤጽ” የሚል ስም አወጣችለት፤


በዘለዓለማዊ ፍቅር በልብህ ውስጥ እንደ ማኅተም አትመኝ፤ በክንድህም እንደ ማኅተም እኔን ብቻ ያዘኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናት፤ ቅናትም እንደ መቃብር የከፋች ናት፤ የእሳትዋ ወላፈን እንደ እግዚአብሔር ወላፈን ነው።


ስለዚህ ሕዝቤ ዕውቀት በማጣታቸው ተማርከው ይወሰዳሉ፤ የተከበሩ መሪዎቻቸው እስከ ሞት ድረስ ይራባሉ፤ ሕዝቡም በውሃ ጥም ይቃጠላል።


ከእንግዲህ ወዲህ “የተተወች” ተብለሽ አትጠሪም፤ ምድርሽም “ባድማ” ተብላ አትጠራም። የምትጠሪበትም አዲስ ስም፥ “እግዚአብሔር በእርስዋ ደስ ይለዋል!” የሚል ይሆናል፤ ምድርሽም “ባለ ባል” ተብላ ትጠራለች፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ ምድርሽም ባል እንዳላት ሴት ትሆናለች።


ከዚያን በኋላ ባላቅ ከፊተኞቹ መልእክተኞች ይበልጥ የተከበሩና ቊጥራቸውም የበዛ ሹማምንት ወደ በለዓም ላከ፤


የአይሁድ መሪዎች ግን የአይሁድ እምነት ተከታዮች የሆኑትን ሀብታሞች ሴቶችና የከተማውን ታላላቅ ሰዎች አሳድመው በጳውሎስና በበርናባስ ላይ ስደት እንዲነሣ አደረጉ፤ ከአገራቸውም አስወጡአቸው።


ስለዚህ ከእነርሱ ብዙዎች አመኑ፤ ብዙዎች የግሪክ ሀብታሞች ሴቶችና ብዙዎች ግሪካውያን ወንዶችም አመኑ።


አቤሜሌክም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ዳዊት ለአንተ የታመነ የጦር መኰንን ነው፤ የአንተው የራስህ ዐማች ከመሆኑም ሌላ የክብር ዘብህ አዛዥ ነው፤ በቤተ መንግሥትህም አደባባይ እንደ እርሱ የሚከበር ማን አለ?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos