ዘፍጥረት 33:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብ ግን ወደ “ሱኮት” ሄደ፥ ከዚያም ለራሱ ቤትን ሠራ፥ ለከብቶቹም ዳሶችን አደረገ። ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም “ሱኮት” ብሎ ጠራው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ፤ እዚያም ለራሱ መጠለያ፣ ለከብቶቹም በረት ሠራ፤ ከዚህም የተነሣ የቦታው ስም ሱኮት ተባለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት አመራ፤ እዚያም ለራሱ ቤትና ለከብቶቹም መጠለያ ሠራ፤ ስለዚህ ያ ስፍራ ሱኮት ተባለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብ ግን በሰፈሩ አደረ፤ በዚያም ለእርሱ ቤትን ሠራ፤ ለከብቶቹም ዳሶችን አደረገ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ማኅደር ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ በዚያም ለእርሱ ቤትን ሠራ ለከብቶች ዳሶችን አደረገ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ሱኮት ብሎ ጠራው። |
በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የተቀረውም የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበር።
የሱኮትንም ሰዎች፥ “የምድያምን ነገሥታት ዜባሕንና ጻልሙናን በማሳደድ ላይ ስለ ሆንኩ የተከተሉኝም ሰዎች ስለ ደከሙ ብኝ እባካችሁ የሚበሉትን እንጀራ ስጧቸው” አላቸው።