Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 33:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት አመራ፤ እዚያም ለራሱ ቤትና ለከብቶቹም መጠለያ ሠራ፤ ስለዚህ ያ ስፍራ ሱኮት ተባለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ፤ እዚያም ለራሱ መጠለያ፣ ለከብቶቹም በረት ሠራ፤ ከዚህም የተነሣ የቦታው ስም ሱኮት ተባለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ያዕቆብ ግን ወደ “ሱኮት” ሄደ፥ ከዚያም ለራሱ ቤትን ሠራ፥ ለከብቶቹም ዳሶችን አደረገ። ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም “ሱኮት” ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ያዕ​ቆብ ግን በሰ​ፈሩ አደረ፤ በዚ​ያም ለእ​ርሱ ቤትን ሠራ፤ ለከ​ብ​ቶ​ቹም ዳሶ​ችን አደ​ረገ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ቦታ ስም ማኅ​ደር ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ በዚያም ለእርሱ ቤትን ሠራ ለከብቶች ዳሶችን አደረገ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ሱኮት ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 33:17
10 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ዔሳው በዚያኑ ቀን ጒዞውን በመጀመር ወደ ኤዶም ተመለሰ።


ንጉሥ ሰሎሞን እነዚህን ሁሉ ያሠራው በዮርዳኖስ ሸለቆ በሱኮትና ጻርታን መካከል በሚገኘው በብረት ማቅለጫ ስፍራ ነበር።


እግዚአብሔር በመቅደሱ ሆኖ እንዲህ አለ፦ “ድል አድርጌ ሴኬምን እሸነሽናለሁ፤ የሱኮትንም ሸለቆ ለሕዝቤ አከፋፍላለሁ።


እስራኤላውያንም ከራምሴ ተነሥተው ወደ ሱኮት ለመሄድ በእግር ጒዞ ጀመሩ፤ የሰዎቹም ብዛት ሴቶችና ልጆች ሳይቈጠሩ ስድስት መቶ ሺህ ነበር።


እስራኤላውያን ከሱኮት ተነሥተው በበረሓው ዳርቻ በምትገኘው በኤታም ሰፈሩ፤


ከዮርዳኖስ ሸለቆ በተለይ የሐሴቦን ንጉሥ የሲሖን መንግሥት ቅሬታ የሆኑትን ቤትሐራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮትና ጻፎን ተብለው የሚጠሩትን ጭምር ያጠቃልላል፤ በምዕራብ በኩል የሚዋሰናቸውም የዮርዳኖስ ወንዝ ሲሆን፥ በሰሜን እስከ ገሊላ ባሕር ይደርሳል።


ከሱኮትም ሰዎች አንዱን ወጣት ይዞ መረመረው፤ ወጣቱም የሱኮትን መሪዎችና ሽማግሌዎች የነበሩትን የሰባ ሰባት ሰዎችን ስም ዝርዝር ጽፎ ሰጠው።


ከዚህ በኋላ እሾኽና አሜከላ ከበረሓ ወስዶ የሱኮትን መሪዎች ገረፋቸው።


ወደ ሱኮት በደረሱም ጊዜ ጌዴዎን ለከተማይቱ ሰዎች እንዲህ አለ፤ “እስቲ ለሰዎቼ እንጀራ ስጡልኝ፤ እነርሱ እጅግ ደክመዋል፤ እኔም ዜባሕና ጻልሙናዕ የተባሉትን የምድያማውያን ነገሥታት በማሳደድ ላይ ነኝ።”


ጌዴዎን ወደ ጵኑኤልም ሄዶ በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ያንኑ ጥያቄ አቀረበላቸው፤ ነገር ግን የጵኑኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች የሰጡትን ተመሳሳይ መልስ ሰጡት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos