ዕዝራ 9:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም ነገር በሰማሁ ጊዜ ልብሴንና ካባዬን ቀደድሁ፥ የራሴን ጠጉርና ጢሜንም ነጨሁ፥ ደንግጬም ተቀመጥሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ይህን በሰማሁ ጊዜ፣ መጐናጸፊያዬንና ካባዬን ቀደድሁ፤ የራሴን ጠጕርና ጢሜን ነጨሁ፤ እጅግ ደንግጬም ተቀመጥሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ይህን በሰማሁ ጊዜ በሐዘን መጐናጸፊያዬንና ካባዬን ቀደድሁ፤ የራስ ጠጒሬንና ጢሜን በመንጨት በብርቱ ሐዘን ላይ ሆኜ ተቀመጥሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ነገር በሰማሁ ጊዜ ልብሴንና መጐናጸፊያዬን ቀደድሁ፤ አዘንሁም፤ የራሴንና የጢሜንም ጠጕር ነጨሁ፤ ደንግጬም ተቀመጥሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ነገር በሰማሁ ጊዜ ልብሴንና መጐናጸፊያዬን ቀደድሁ፤ የራሴንና የጢሜንም ጠጉር ነጨሁ፤ ደንግጬም ተቀመጥሁ። |
ከዚህ በኋላ ኤልያቄምና ሼብና እንዲሁም ዮአሕ በኀዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ቀርበው የአሦራውያን ባለ ሥልጣን የተናገረውን አስረዱት።
ከእነርሱም ጋር ተከራከርሁ፥ ረገምኋቸውም፥ ከእነርሱም አያሌዎቹን መታሁ፥ ጠጉራቸውንም ነጨሁ፥ እንዲህም ብዬ በእግዚአብሔር አማልኋቸው፦ ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለእናንተና ለልጆቻችሁ አትውሰዱ።
ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባውና በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቷል።
ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በጌታ ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።