ዕዝራ 9:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 አንዳንድ ሴቶች ልጆቻቸውን ለራሳቸውና ለወንዶች ልጆቻቸው ሚስት አድርገው ወስደዋል፥ ቅዱሱንም ዘር ከምድር ሕዝቦች ጋር ደባልቀዋል፤ በዚህ አለመታመን የአለቆቹና የባለሥልጣኖቹ እጅ ቀዳሚ ነበር።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ሴቶቻቸውን ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ሚስት አድርገው ወስደዋል፤ የተቀደሰውንም ዘር ከምድር ሕዝቦች ጋራ ደባልቀዋል፤ በዚህ በደል ዋነኛ የሆኑትም መሪዎቹና ሹማምቱ ናቸው።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ሚስቶች የሚሆኑ ከእነዚያ ወገኖች አግብተዋል፤ አጋብተዋልም፤ ቅዱሱን ዘር ከሌሎች ከአካባቢው አሕዛብ ጋር ቀላቅለዋል፤ በዚህ እምነተ ቢስ በሆነ ተግባር መሪዎቹና ባለ ሥልጣኖቹ ግንባር ቀደም ሆነዋል።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ለራሳቸውና ለልጆቻቸውም ሴቶች ልጆቻቸውን ወስደዋል፤ የተቀደሰውንም ዘር ከምድር አሕዛብ ጋር ደባልቀዋል፤ አስቀድሞም አለቆቹና ሹሞቹ በዚህ መተላለፍ መጀመሪያ ሆነዋል” አሉኝ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ለራሳቸውና ለልጆቻቸውም ሴቶች ልጆቻቸውን ወስደዋል፤ የተቀደሰውንም ዘር ከምድር አሕዛብ ጋር ደባልቀዋል፤ አስቀድሞም አለቆቹና ሹማምንቶቹ በዚህ መተላለፍ መጀመሪያ ሆነዋል” አሉኝ። Ver Capítulo |