የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ መላ ሠራዊቱን በአንድነት ሰበሰበ፤ ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ባሉአቸው ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ተደግፎ በመዝመት የእስራኤል ዋና ከተማ የሆነችውን ሰማርያን ከቦ አደጋ ጣለባት።
ዕዝራ 7:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ ለሰማያት አምላክ ሕግ ጸሐፊ ለካህኑ ዕዝራ፤ አሁንም አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ፤ ለሰማይ አምላክ ሕግ መምህር ለሆነው ለካህኑ ለዕዝራ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ፥ የሰማይ አምላክ የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናት ረገድ ታላቅ ምሁር ለሆነው ለካህኑ ዕዝራ፦ ሰላም ላንተ ይሁን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከንጉሠ ነገሥት ከአርተሰስታ ለሰማይ አምላክ ሕግ ጸሓፊ ለካህኑ ለዕዝራ፥ ሰላም ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “ከንጉሠ ነገሥት ከአርጤክስስ ለሰማይ አምላክ ሕግ ጸሐፊ ለካህኑ ለዕዝራ፥ ሙሉ ሰላም ይሁን፤ |
የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ መላ ሠራዊቱን በአንድነት ሰበሰበ፤ ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ባሉአቸው ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ተደግፎ በመዝመት የእስራኤል ዋና ከተማ የሆነችውን ሰማርያን ከቦ አደጋ ጣለባት።
ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለውን ምድር ሁሉ ከቲፍሳሕ ከተማ ጀምሮ እስከ ጋዛ ከተማ ድረስ ይገዛ ነበር፤ ይህም ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ የሚገኙትን ነገሥታትን ሁሉ ያጠቃልላል፤ ጐረቤቱ ከሆኑት አገሮችም ሁሉ ጋር በሰላም ይኖር ነበር።
የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ “የሰማያት አምላክ ጌታ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፥ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል፤
ንጉሡ እንዲህ የሚለውን መልስ ላከ፦ “ለአዛዡ ለሬሑምና ለጸሐፊውም ለሺምሻይ፥ በሰማርያና በወንዝ ማዶ ባለ አገር ለተቀመጡ ለቀሩት ተባባሪዎቻቸው ሰላም! አሁንም
የጌታን ትእዛዝ ቃልና ለእስራኤል የሆነውን ሥርዓት ይጽፍ ለነበረው ለጸሐፊው ለካህኑ ለዕዝራ ንጉሡ አርጤክስስ የሰጠው የደብዳቤው ግልባጭ ይህ ነው፦
ይህ ዕዝራ ከባቢሎን መጣ፥ የእስራኤል አምላክ ጌታ ለሙሴ በሰጠው ሕግ ችሎታ ያለው ጸሐፊ ነበረ፤ የአምላኩ የጌታ እጅ በእርሱ ላይ ስለ ነበረች ንጉሡ የጠየቀውን ነገር ሁሉ ሰጠው።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነዖርን ከፈረሶች፥ ከሰረገሎች፥ ከፈረሰኞች፥ ከጉባኤና ከብዙ ሕዝብ ጋር በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉት የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ናቸው።”