Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 1:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ “የሰማያት አምላክ ጌታ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፥ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፤ “ ‘የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳ በምትገኘው በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እንድሠራለት አዝዞኛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የፋርስ ንጉሠ ነገሥትም በዐዋጅ የሰጠው ትእዛዝ እንዲህ የሚል ነበር፦ “የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የዓለም ሁሉ ገዢ አድርጎኛል፤ እርሱም ቤተ መቅደስን በይሁዳ ምድር በምትገኘው በኢየሩሳሌም እንድሠራለት አዞኛል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዲህ ይላል፦ የሰ​ማይ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ርን መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ሰጥ​ቶ​ኛል፤ በይ​ሁ​ዳም ባለ​ችው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤትን እሠ​ራ​ለት ዘንድ እን​ዳ​ስብ አደ​ረ​ገኝ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 “የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል ‘የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እሠራለት ዘንድ አዝዞኛል፤

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 1:2
34 Referencias Cruzadas  

“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ!


እንዲሁም ኪራም እንዲህ አለ፦ “ሰማይንና ምድርን የፈጠረ፥ ለጌታም ቤተ መቅደስ ለመንግሥቱም ቤተ መንግሥት እንዲሠራ ጥበበኛና ብልሃተኛ አስተዋይም ልጅ ለንጉሡ ለዳዊት የሰጠ የእስራኤል አምላክ ጌታ ቡሩክ ይሁን።


እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው የይሁዳና የብንያም የአባቶች አለቆች፥ ካህናቱና ሌዋውያኑም ሁሉ ለመሄድና በኢየሩሳሌም ያለውን የጌታን ቤት ለመሥራት ተዘጋጁ።


ለጠራቢዎችና ለአናጢዎችም ገንዘብ ሰጡ፤ የፋርስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀደላቸው የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ ወደ ያፎ ባሕር እንዲያመጡ ለሲዶናውያንና ለጢሮሳውያን መብልና መጠጥ ዘይትም ሰጡ።


ዘሩባቤል፥ ኢያሱና የቀሩትም የእስራኤል አባቶች አለቆች፦ “የአምላካችንን ቤት ማነፅ ለእኛና ለእናንተ አይደለም፥ እኛ ለብቻችን ሆነን ንጉሥ ቂሮስ የፋርስ ንጉሥ እንዳዘዘን ለጌታ ለእስራኤል አምላክ ቤት እንገነባለን” አሉአቸው።


እነዚህን ዕቃዎች ውሰድ፥ በኢየሩሳሌምም ባለው መቅደስ አስቀምጠው የእግዚአብሔርም ቤት በስፍራው ይሠራ’” አለው።


ይህም ለሰማያት አምላክ መልካም መዓዛ እንዲያቀርቡ፥ ለንጉሥና ለልጆቹ ሕይወትም እንዲጸልዩ ነው።


በንጉሡ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ በኢየሩሳሌም ስላለው ስለ እግዚአብሔር ቤት እንዲህ ብሎ አዘዘ፥ መሥዋዕት የሚሠዋበት ቦታ፥ ይህ ቤት ይሠራ፥ በጽኑም ይመሥረት፤ ርዝመቱ ስድሳ ክንድ ስፋቱም ስድሳ ክንድ ይሁን።


“ከንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ ለሰማያት አምላክ ሕግ ጸሐፊ ለካህኑ ዕዝራ፤ አሁንም


እነዚህን ቃላት በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ። ለብዙ ቀኖች አዘንሁ፤ በሰማይ አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥


እንዲህም አልሁ፦ ታላቅና የተፈራ አምላክ፥ ለሚወድዱትና ትእዛዙን ለሚጠብቁ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የሚጠብቅ፥ የሰማይ አምላክ ጌታ ሆይ፥


የሰማይን አምላክ አመስግኑ፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።


አቤቱ፥ ምድርህን በመልካም ጎበኘህ፥ የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።


የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በጌታ እጅ ነው፥ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።


ከምሥራቅ አንዱን ያስነሣ፥ በጽድቅም ወደ እግሩ የጠራው ማን ነው? አሕዛብንም አሳልፎ በፊቱ ሰጠው፥ ነገሥታትንም አስገዛለት፤ ለሰይፉ እንደ ትቢያ ለቀስቱም እንደ ተጠረገ እብቅ አድርጎ ሰጣቸው።


የባርያዬን ቃል አጸናለሁ፤ የመልእክተኞቼንም ምክር እፈጽማለሁ፤ ኢየሩሳሌምን፦ የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፥ የይሁዳንም ከተሞች፦ ትታነጻላችሁ ፍራሾቻችሁንም አቆማለሁ እላለሁ።


ቂሮስንም፦ “እርሱ እረኛዬ ነው”፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፦ “ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል” ይላል፤ እኔም “ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል” እላለሁ።


ጌታ ለቀባው፥ አሕዛብንም በፊቱ እንዲገዙለት፥ የነገሥታትንም ወገብ እዲፈታ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹ በፊቱ እንዲከፈቱለት፥ ቀኝ እጁን ለያዘው ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦


ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድነው?


እናንተም፦ “ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ” ትሉአቸዋላችሁ።


ምድሪቱን በምድርም ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ለዓይኔም መልካም ለሆነው እሰጣታለሁ።


“ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህችም ስፍራ እናንተን በመመለስ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።


እርሱም፦ “እኔ ዕብራዊ ነኝ፥ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን፥ የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos