ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፦ “ተነሣ፥ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፥ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፋ” እያሉ ያስቸኩሉት ነበር።
ሕዝቅኤል 7:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድር የምትኖር ሆይ፥ ፍጻሜህ ወደ አንተ መጥቷል፥ ጊዜው መጥቷል፥ ቀኑ ቀርቧል፥ የሽብር ነው እንጂ በተራራ ላይ ያለ እልልታ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በምድሪቱ የምትኖሩ ሆይ፤ የጥፋት ፍርድ መጥቶባችኋል፤ ጊዜው ደርሷል፤ በተራሮች ላይ እልልታ ሳይሆን ሽብር የሚሰማበት ቀን ቀርቧል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድሪቱ የምትኖሩ ሕዝብ ሁሉ የመጥፊያችሁ ጊዜ ደርሶአል፤ ጊዜው ደርሶአል፤ ቀኑም ቀርቦአል፤ እርሱም የሁከት ቀን ነው እንጂ በከፍተኛ ቦታዎች የመፈንጠዣ ቀን አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሀገር የምትኖር ሆይ! ስብራትህ ጊዜው ደረሰ፤ ቀኑም ቀረበ፤ የሽብር ቀን ነው እንጂ የተራራ ላይ ዕልልታ አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር የምትቀመጥ ሆይ፥ ተራህ ደርሶአል፥ ጊዜ መጥቶአል፥ ቀን ቀርቦአል፥ የሽብር ቀን ነው እንጂ በተራራ ላይ ያለ እልልታ አይደለም። |
ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፦ “ተነሣ፥ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፥ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፋ” እያሉ ያስቸኩሉት ነበር።
ደስታና ሐሴትም ከፍሬያማው እርሻ ተወስዶአል፤ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና እልልታ የለም፤ በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ።
ስለዚህም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የምናገረው ቃል ይፈጸማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚዘገይ የለም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“እነሆ፥ ተራሮችን የሠራ፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ የልቡንም ሐሳብ ለሰው የሚነግር፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ ጌታ ነው።”
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአል፤ በቅድሚያም በእኛ የሚጀመር ከሆነ፥ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?