ሕዝቅኤል 38:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳባ፥ ድዳን፥ የተርሴስ ነጋዴዎች፥ መንገዶችዋም ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ ምርኮን ትማርክ ዘንድ መጥተሃልን? ብዝበዛንስ ትበዘብዝ ዘንድ ብርንና ወርቅንስ ትወስድ ዘንድ ከብትንና ዕቃንስ ትወስድ ዘንድ እጅግስ ብዙ ምርኮ ትማርክ ዘንድ ወገንህን ሰብስበሃልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳባና ድዳን፣ የተርሴስ ነጋዴዎችና መንደሮቿም ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፤ “ልትዘርፍ መጣህን? ሰራዊትህን ያሰባሰብኸው ለመበዝበዝ፣ ወርቅና ብሩን አጋብሶ ለመሄድ፣ ከብቱንና ሸቀጡን ለመውሰድ፣ ብዙ ምርኮ ይዞ ለመመለስ ነውን?” ’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳባና ዴዳን፥ እንዲሁም የተርሴስ ነጋዴዎችና ወጣት ጦረኞች እንዲህ ይሉሃል፦ ‘ምርኮን ለመውሰድ መጣህን? ብርንና ወርቅን፥ እንስሶችና ቈሳቊስን፥ ማለት ብዙ ምርኮን እንዲያጓጒዙልህ ብዛት ያላቸውን ሰዎችህን ሰበሰብክን?’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳባና ድዳን፥ የተርሴስም ነጋዴዎች፥ መንደሮችዋም ሁሉ፦ ምርኮን ትማርክ ዘንድ መጥተሃልን? ብዝበዛንስ ትበዘብዝ ዘንድ፥ ብርንና ወርቅንስ ትወስድ ዘንድ፥ ከብትንና ዕቃንስ ትወስድ ዘንድ፥ እጅግስ ብዙ ምርኮ ትማርክ ዘንድ ወገንህን ሰብስበሃልን? ይሉሃል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳባና ድዳን የተርሴስም ነጋዴዎች መንገዶችዋም ሁሉ፦ ምርኮን ትማርክ ዘንድ መጥተሃልን? ብዝበዛንስ ትበዘብዝ ዘንድ ብርንና ወርቅንስ ትወስድ ዘንድ ከብትንና ዕቃንስ ትወስድ ዘንድ እጅግስ ብዙ ምርኮ ትማርክ ዘንድ ወገንህን ሰብስበሃልን? ይሉሃል። |
ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፤ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፤ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤ በሚያስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።
ገመዶችህ ላልተዋል፥ ችካላቸውንም አልጸናም፥ ሸራውንም መወጠር አልቻሉም። በዚያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ሀብት ይከፋፈላል፤ አንካሶች እንኳ ከክፍፍሉ ይደርሳቸዋል።
እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኤዶምያስ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከእርሷም ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማን ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።
የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።