ሕዝቅኤል 35:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዘለዓለም ባድማ አደርግሃለሁ፥ ከተሞችህም ሰው አይኖርባቸውም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዘላለም ባድማ አደርግሃለሁ፤ ከተሞችህ መኖሪያ አይሆኑም። ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ለዘለዓለሙ ምድራችሁን ባድማ አደርጋለሁ፤ ዳግመኛም በከተሞቻችሁ የሚኖር አይገኝም፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዘለዓለምም ባድማ አደርግሃለሁ፤ ከተሞችህም ሰው የማይኖርባቸው ይሆናሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዘላለምም ባድማ አደርግሃለሁ ከተሞችህም ሰው የማይኖርባቸው ይሆናሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። |
እንዲህ በል፦ ‘አቤቱ፥ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፥ ለዘለዓለምም ባድማ እንድትሆን ልታጠፋት በዚህች ስፍራ ላይ አንተ ተናግረሃል።’
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኤዶምያስ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከእርሷም ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማን ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።
ኤዶምያስ እና ነገሥታቶችዋ አለቆችዋም ሁሉ በዚያ አሉ፤ ኃይል የነበራችው በሰይፍ ከተገደሉት፥ ካልተገረዙት እና ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተኝተዋል።
ሰውንና እንስሳም በእናንተ ላይ አበዛለሁ፥ እነርሱም ይበዛሉ ያፈራሉም፤ እንደ ቀድሞም ሰዎችን አኖርባችኋለሁ፥ መጀመሪያ ካደረግሁላችሁ ይልቅ መልካም አደርግላችኋለሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
ጅማትንም አደርግላችኋለሁ፥ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ ቆዳ አለብሳችኋለሁ፥ በውስጣችሁ እስትንፋስ አገባባችኋለሁ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
እጄንም በእነሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በሚኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ምድሪቱን ከዲብላ ምድረ በዳ ይልቅ ውድማና በረሃ አደርጋታለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
ዓይኔ አይራራልሽም እኔም አላዝንም፤ መንገድሽን በአንቺ ላይ እመልስብሻለሁ፥ ርኩሰቶችሽም በመካከልሽ ይሆናሉ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
ዓይኔም አይራራም፥ እኔም አላዝንም፥ መንገድሽን በአንቺ ላይ እመልስብሻለሁ፥ ርኩሰቶችሽም በመካከልሽ ይሆናሉ፥ የምቀሥፍም እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ ይሆናሉ፥ አረም እንደ ዋጠው ስፍራና እንደ ጨው ጉድጓድ ለዘለዓለምም ይጠፋሉ፤ የሕዝቤም ትሩፍ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።