በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልዕክተኞችን፥ የዝግባ ዕንጨት፥ አናጢዎችንና ድንጋይ ጠራቢዎችንም ላከ፥ ለዳዊት ቤተ መንግሥት ሠሩለት።
ሕዝቅኤል 26:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልጅ ሆይ ጢሮስ በኢየሩሳሌም ላይ፦ “እሰይ የሕዝቦች በር የነበረች ተሰበረች፤ ወደ እኔም ተመለሰች፤ እርሷ ስለፈረሰች እኔ እሞላለሁ፤” ብላለችና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰው ልጅ ሆይ! ጢሮስ ስለ ኢየሩሳሌም፣ ‘ዕሠይ! የሕዝቦች በር ተሰበረች፤ ደጆቿም ወለል ብለው ተከፈቱልኝ፤ እንግዲህ እርሷ ስለ ፈራረሰች እኔ እከብራለሁ’ ብላለችና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰው ልጅ ሆይ! በጢሮስ ከተማ ያሉ ሕዝቦች የሚደሰቱበት ነገር ይህ ነው፦ ‘ኢየሩሳሌም ፈራርሳለች! የንግድ ኀይልዋም ወድቋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከእኛ ጋር መወዳደር ከቶ ስለማትችል እኛ እንበለጽጋለን’ ይላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢየሩሳሌም ላይ፦ እሰይ፥ ተሰበረች፥ ጠፋችም፥ ሕዝቧም ወደ እርስዋ ተመለሱ፤ ሞልታ የነበረች አለቀች ብላለችና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢየሩሳሌም ላይ፦ እሰይ፥ የአሕዛብ በር የነበረች ተሰብራለች ወደ እኔም ተመልሳለች፥ እርስዋ ፈርሳለችና እኔ እሞላለሁ ብላለችና |
በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልዕክተኞችን፥ የዝግባ ዕንጨት፥ አናጢዎችንና ድንጋይ ጠራቢዎችንም ላከ፥ ለዳዊት ቤተ መንግሥት ሠሩለት።
ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፥ ወደ ሞዓብም ንጉሥ፥ ወደ አሞንም ልጆች ንጉሥ፥ ወደ ጢሮስም ንጉሥ፥ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ትልካቸዋለህ።
ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለመደምሰስ የተረፉትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና ለማጥፋት ስለሚመጣው ቀን ነው፤ ጌታ ፍልስጥኤማውያንና የከፍቶርን ደሴት ትሩፍ ያጠፋልና።
ስለ አሞን ልጆች፤ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ለእስራኤል ልጆች የሉትምን? ወይስ ወራሽ የለውምን? ታዲያ ሚልኮምስ ጋድን ለምን ወረሰ? ሕዝቡስ በከተሞቹ ላይ ለምን ተቀመጠ?
አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! በአሕዛብ መካከል ታላቅ የነበረች እንደ መበለት ሆናለች፥ በአውራጆች መካከል ልዕልት የነበረች ተገዢ ሆናለች።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእስራኤል ምድር ላይ በውስጥሽ ባለው ንቀት ሁሉ ደስ ብሎሽ በእጅሽ አጨብጭበሻልና፥ በእግርሽም አሸብሽበሻልና፥
ጢሮስና ሲዶና የፍልስጥኤምም ግዛት ሁሉ ሆይ፥ ከእናንተ ጋር ምን ጉዳይ አለኝ? በውኑ ልትበቀሉኝ ትፈልጋላችሁን? በቀልን በእኔ ላይ ማውረድ ብትሞክሩ፥ በቀሉን መልሼ በፍጥነት በእናንተ ላይ አወርደዋለሁ።