La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 2:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሲያናግረኝም መንፈስ ገባብኝ፥ በእግሬም አቆመኝ፥ የሚናገረኝንም ሰማሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም ሲናገር፣ መንፈስ ወደ ውስጤ ገብቶ በእግሬ አቆመኝ፤ ሲናገረኝም ሰማሁት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በተናገረኝም ጊዜ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጤ ገብቶ በእግሮቼ አቆመኝ፤ የሚናገረኝንም ሰማሁ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በተ​ና​ገ​ረ​ኝም ጊዜ መን​ፈስ በእኔ ላይ መጣ፤ አነ​ሣ​ኝም፤ በእ​ግ​ሬም አቆ​መኝ፤ የሚ​ና​ገ​ረ​ኝ​ንም ሰማሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በተናገረኝም ጊዜ መንፈስ ገባብኝ በእግሬም አቆመኝ፥ የሚናገርኝንም ሰማሁ።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 2:2
13 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ብዙ ዓመታት ታገሥሃቸው፥ በነቢያትህም እጅ በመንፈስህ መሰከርክባቸው፥ አላደመጡም፥ ስለዚህም በምድር አሕዛብ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው።


የጌታም መንፈስ ወደቀብኝ እንዲህም አለኝ፦ ጌታ እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህን ነገር ተናግራችኋል፥ እኔ የልባችሁን ሐሳብ አውቃለሁና።


ለዓመፀኛውም ቤት ምሳሌን ተናገር፥ እንዲህም በላቸው፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣደው፥ ድስቱን ጣደው፥ ውኃም ጨምርበት።


መንፈስም አነሣኝ፥ ከኋላዬም የጌታ ክብር ከሥፍራው ይባረክ የሚል ታላቅ የሚያጉረመርም ድምፅ ሰማሁ።


መንፈስ አነሳኝ፥ ወሰደኝም፥ እኔም በምሬትና በመንፈሴ ቁጣ ሄድሁ፥ የጌታም እጅ በላዬ ላይ በርትታ ነበር።


መንፈስም ገባብኝ፥ በእግሬም አቆመኝ፥ ተናገረኝም እንዲህም አለኝ፦ ሂድ፥ በቤትህ ውስጥ ዘግተህ ተቀመጥ።


መንፈሴን በውስጣችሁ አኖራለሁ፥ በትእዛዜ እንድትሄዱና ፍርዴን እንድትጠብቁ አደርጋችኋለሁ ትፈጽሟቸዋላችሁም።


ከሦስቱ ቀን ተኩልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፤ በእግሮቻቸውም ቆሙ፤ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው።


የጌታም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ሳለ ያነቃቃው ጀመር።


ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያ ቀን ጀምሮ የጌታ መንፈስ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ፤ ሳሙኤልም ወደ ራማ ተመለሰ።