ሕዝቅኤል 17:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዓመፀኛ ቤት እንዲህ በል፦ እነዚህ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ አታውቁምን? በላቸው። ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና ልዑሎችዋን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ባቢሎን አመጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለዚህ ዐመፀኛ ቤት እንዲህ በል፤ ‘የእነዚህ ነገሮች ትርጕም ምን እንደ ሆነ አታውቁምን?’ እንዲህ በላቸው፤ ‘የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ ንጉሧንና መሳፍንቷን ማረከ፤ ወደ ባቢሎንም ይዟቸው ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የምሳሌውን ትርጒም ያውቁ እንደ ሆነ እስቲ እነዚህን ዐመፀኞች ጠይቃቸው፤ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ንጉሡንና መሳፍንቱን ወደ ባቢሎን የወሰዳቸው መሆኑን ንገራቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሰው ልጅ ሆይ፥ ለአስቈጡኝ ለእስራኤል ቤት ይህ ትርጓሜ ምን እንደ ሆነ አታውቁምን? በላቸው። እንዲህም ብለህ ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ ንጉሥዋንና መኳንንቶችዋንም ማረከ፤ ወደ ሀገሩም ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዓመፀኛ ቤት፦ ይህ ትርጓሜ ምን እንደ ሆነ አታውቁምን? በላቸው። እንዲህም ብለህ ንገራቸው፦ እነሆ፥ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና መኳንንቶችዋንም ማረከ፥ ወደ እርሱም ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው። |
የይሁዳንም ንጉሥ ሴዴቅያስንና አለቆቹን፥ ለጠላቶቻቸው እጅ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ ከእናንተም ለተመለሱት ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ።
በእርግጥ ከጌታ ቁጣ የተነሣ ከፊቱ አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆነ፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።
እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትልቅ ክንፎች፥ ረጅም ማርገብገቢያ ያለው፥ ዝንጉርጉርና ብዙ ላባ ያለው ትልቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጣ፥ የዝግባንም ጫፍ ወሰደ።
ይህም በመካከላችሁ ምልክት ይሆናል፤ ልጆቻችሁም በሚመጣው ዘመን፦ ‘ለእናንተ እነዚህ ድንጋዮች የሚሰጡት ትርጒም ምንድነው?’ ብለው ሲጠይቁአችሁ፥