ዘፀአት 39:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅደሱ ለማገልገል ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ በብልሃት የተሠራ ልብስ አደረጉ፥ ጌታም ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለአሮን የተቀደሱ ልብሶችን ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመቅደሱ አገልግሎት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ የተፈተሉ ልብሶችን ሠሩ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለአሮን የተቀደሱ ልብሶችን ሠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ ሲያገለግሉ የሚለብሱአቸውን እጅግ የተዋቡትን የካህናት ልብሶች ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ሠሩ፤ የአሮንንም የክህነት ልብሶች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀረውም የመባ ወርቅ በእግዚአብሔር ፊት ይሠሩበት ዘንድ ንዋየ ቅድሳት ሆኖ ተሠራ። ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም ከቀይ ግምጃም ለመቅደሱ አገልግሎት ልብሶችን ሠሩ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለአሮን የተቀደሰውን ልብስ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ በመቅደሱ ለማገልገል ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይ ግምጃም በብልሃት የተሠራ ልብስ፥ ለአሮንም የተቀደሰውን ልብስ አደረጉ። |
“ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠሩ ዐሥር መጋረጆች ያሉበትን ድንኳን ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።
በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት እንዲያገለግሉበት የተቀደሱትን የካህኑን የአሮን ልብሶችና የልጆቹን ልብሶች።”
በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን እግሮች፥ የአደባባዩን መግቢያ እግሮች፥ የማደሪያውን ካስማዎች ሁሉና በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን ካስማዎች ሁሉ ሠራ።
በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነትም እንዲያገለግሉበት የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶችና የልጆቹን ልብሶች አመጡ።
ካህናቱም ከገቡ በኋላ የሚያገለግሉበትን ልብስ ሳያወልቁ ከመቅደሱ ወደ ውጭው አደባባይ አይወጡም፥ የተቀደሱ ናቸውና፤ ወደ ሕዝቡ ቦታ ሲቀርቡ ሌላ ልብስ መልበስ አለባቸው።