ዘፀአት 3:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ቃልህን ይሰማሉ፤ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብጽ ንጉሥ ትሄዳላችሁ፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ጌታ ተገለጠልን፤ ስለዚህ ለአምላካችን ለጌታ እንድንሠዋ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንሂድ’ ትሉታላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእስራኤል አለቆችም ይሰሙሃል። አንተና የእስራኤል አለቆች ወደ ግብጽ ንጉሥ ትሄዱና፣ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ተገለጠልን፤ ስለዚህም ወደ ምድረ በዳ የሦስት ቀን መንገድ ተጕዘን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንድናቀርብ ፍቀድልን’ ብላችሁ ትነግሩታላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሕዝቤም አንተ የምትነግራቸውን ሁሉ ይሰማሉ፤ ከዚያም በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ አለቆች ጋር ሆነህ ወደ ግብጽ ንጉሥ ሂድና ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ተገልጦልናል፤ ስለዚህም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ተጒዘን ወደ በረሓ እንድንሄድ ፍቀድልን’ ብላችሁ ንገሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ቃልህን ይሰማሉ፤ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ትገባላችሁ፦ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ጠርቶናል፤ አሁንም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንሠዋ ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ወደ ምድረ በዳ እንሄዳለን ትሉታላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ቃልህን ይሰማሉ፤ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ትገባላችሁ፤ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ተገለጠልን፤ አሁንም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንሠዋ ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንሂድ’ ትሉታላችሁ። |
አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው፥ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የባሉጥ ዛፎች አጠገብ ይኖር ነበር፥ እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።
ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፥ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፥ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።
ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ እንዲህም አሉት፦ “የዕብራውያን አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በፊቴ እራስህን ለማዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ።
በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ፤ የእስራኤልንም ልጆች እንድታዝዝ የምሰጥህን ነገር ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛው ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ።
እርሱም፦ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ይሆናል፤ ሕዝቡን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታገለግላላችሁ” አለ።
ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ትሰበስባለህ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ “ጌታ የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ፥ የያዕቆብም ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ ‘ጎበኘኋችሁ፥ በግብጽም የሚደረግባችሁን አየሁ፤
ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፥ ታደቀዋለህም፥ ከእርሱም ወስደህ አንተን በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። ለእናንተም ፍጹም ቅዱስ ይሆንላችኋል።
ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ።’”
እነርሱም፦ “የዕብራውያን አምላክ ተገናኘን፤ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንድንሄድ፥ ለጌታ ለአምላካችን እንድንሠዋ እንለምንሃለን ካልሆነ ተላላፊ በሽታ ወይም ሰይፍ እንዳይጥልብን” አሉት።
እንዲህም ትለዋለህ፦ ‘ጌታ የዕብራውያን አምላክ፦ በምድረ በዳ እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ፥ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነሆ አንተ እስከ ዛሬ አልሰማህም።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን ‘በትርህን ይዘህ እጅህን በፈሳሾቹ በወንዞቹና በኩሬዎቹ ላይ እጅህን ዘርጋ፥ በግብጽም ምድር ላይ እንቁራሪቶችን አውጣ’ በለው።”
ጌታም እንዲሁ አደረገ፤ በፈርዖን ቤት፥ በአገልጋዮቹም ቤቶች ውስጥ ብዙ የዝንብ መንጋ መጣ፤ በግብጽም ምድር ሁሉ ላይ፤ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ምድር ተበላሸች።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ማልደህ ተነሣ፥ በፈርዖንም ፊት ቁም እንዲህም በለው፦ የዕብራውያን አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ።
ጽድቅን የሚያደርገውን፥ በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እኛ ኃጢአት ሠራን፤ እነሆ፥ አንተ ተቈጥተህ ነበር፤ ፊትህን ስለሰወርክብን እኛ ተሳሳትን።
“ሂድ፥ በኢየሩሳሌም ጆሮዎች ላይ አውጅ፥ እንዲህም በል፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ጽኑ ፍቅር የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስታውሼዋለሁ።
እነርሱም፦ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳም በባድማ ጉድጓድም ባለበት ምድር፥ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን ጌታ ወዴት አለ?’ አላሉም።