Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 14:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው፥ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የባሉጥ ዛፎች አጠገብ ይኖር ነበር፥ እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚህም ያመለጠ አንድ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ይህን ነገረ፤ አብራም በዚያ ጊዜ ይኖር የነበረው በአሞራዊው መምሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ ነበር። መምሬ፣ ወንድሞቹ ኤስኮልና አውናን የአብራም የኪዳን አጋሮቹ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ነገር ግን አንድ ሰው ሸሽቶ መጣና የሆነውን ሁሉ ለዕብራዊው ለአብራም ነገረው፤ በዚያን ጊዜ አብራም የሚኖረው በአሞራዊው መምሬ የተቀደሱ የወርካ ዛፎች አጠገብ ነበር፤ መምሬና ወንድሞቹ ኤሽኮል፥ ዐኔር የአብራም የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከአ​መ​ለ​ጡ​ትም አንድ ሰው መጣ፤ ለዕ​ብ​ራ​ዊው ለአ​ብ​ራ​ምም ነገ​ረው፤ እር​ሱም የኤ​ስ​ኮል ወን​ድ​ምና የአ​ው​ናን ወን​ድም በሆነ በአ​ሞ​ራ​ዊው የመ​ምሬ ዛፍ ይኖር ነበር፤ እነ​ዚ​ያም ከአ​ብ​ራም ጋር ቃል ኪዳን ገብ​ተው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አንድ የሸሸ ስውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የአድባር ዛፍ ይኖር ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 14:13
23 Referencias Cruzadas  

ሌሎቹም የከነዓን ዘሮች ኢያቡሳውያን፥ አሞራውያን፥ ጌርጌሳውያን፥


አብራምም ድንኳኑን ነቀለ መጥቶም በኬብሮን ባለው በመምሬ የባሉጥ ዛፎች ተቀመጠ፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ።


በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የባሉጥ ዛፎች አጠገብ ተገለጠለት።


አብርሃምም፦ “እኔ እምላለሁ” አለ።


አብርሃምም በጎችንና ላሞችን አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፥ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ።


በቤርሳቤህም ቃል ኪዳንን አደረጉ። አቢሜሌክና የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት የሠራዊቱ አለቃ ፊኮልም ተነሥተው ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ።


የቤት አገልጋዮቿን ጠራች፤ እንዲህም አለቻቸው፤ “አያችሁ፤ ለካስ ይህ ዕብራዊ የመጣው መሣለቂያ ሊያደርገን ኖሮአል! እዚህ ድረስ ሰተት ብሎ ገብቶ ካልተኛሁሽ አለኝ፤ እኔም ጩኸቴን ለቀቅሁት፤


ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት በአፈና ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት የተጣልሁት አንዳች ጥፋት ኖሮብኝ አይደለም።”


በዚያን ጊዜ የዘበኞች አለቃ አገልጋይ የሆነ አንድ ዕብራዊ ወጣት ከእኛ ጋር እስር ቤት ነበር። ሕልማችንን በነገርነው ጊዜ፥ ፍቺውን ነገረን፤ ለእያንዳንዳችንም እንደ ሕልማችን ተረጐመልን፤


ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት፤ ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ግብፃውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ነበር።


የሳባ ሰዎች አደጋ ጣሉና ወሰዱአቸው፥ ብላቴኖቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ” አለው።


በነዚያም ቀኖች፥ ሙሴ ባደገ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ፥ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፤ የግብጽም ሰው ከወንድሞቹ አንድ የሆነውን ዕብራዊ ሰው ሲመታ አየ።


በከፈተችውም ጊዜ ሕፃኑን አየች፥ እነሆም ሕፃኑ ያለቅስ ነበር፤ አዘነችለትም፦ “ይህ ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው” አለች።


እነርሱም ቃልህን ይሰማሉ፤ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብጽ ንጉሥ ትሄዳላችሁ፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ጌታ ተገለጠልን፤ ስለዚህ ለአምላካችን ለጌታ እንድንሠዋ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንሂድ’ ትሉታላችሁ።


አዋጁም፦ ሰው ሁሉ ዕብራዊ የሆነውን ወንድ ባርያውንና ዕብራዊት የሆነችውን ሴት ባርያውን አርነት እንዲያወጣ፥ አይሁዳዊ ወንድሙንም ማንም እንዳይገዛ የሚል ነው።


እርሱም፦ “እኔ ዕብራዊ ነኝ፥ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን፥ የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ” አላቸው።


ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጡ፥ ከዚያም ከወይኑ አንድ ሙሉ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፥ ከእነርሱም ሁለት ሰዎች በመሎጊያ ተሸከሙት፤ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ።


እስራኤልም እንዲህ ብሎ መልእክተኞችን ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን ላከ፦


እነርሱ ዕብራውያን ናቸው? እኔም ነኝ፤ የእስራኤል ወገን ናቸው? እኔም ነኝ፤ የአብርሃም ዘር ናቸውን? እኔም ነኝ፤ የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸው?


በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይኑር።


የፍልስጥኤም ጦር አዛዦችም እነርሱን ባዩ ጊዜ “እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን ይሠራሉ?” ሲሉ ጠየቁ፤ አኪሽም፥ “ይህ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ የነበረው ዳዊት አይደለምን? ከእኔ ጋር መኖር ከጀመረ እነሆ ዓመት አለፈው፤ እኔን ከተጠጋበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ምንም በደል አላገኘሁበትም” አላቸው።


አንድ የብንያም ወገን የሆነ ሰው ልብሱን ቀዶ፥ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ፥ ከጦሩ ሜዳ እየበረረ ወደ ሴሎ መጣ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos